Wolaita Sodo Regional Veterinary Laboratory

Wolaita Sodo Regional Veterinary Laboratory Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Sodo Regional Veterinary Laboratory, Veterinarian, Wolayta, Sodo.

በክልላችን ተንሠራፍተዉ የሚገኙ መደበኛ፣ ድንበር ዘለልና ተዛማች የሆኑ የእንስሳት በሽታዎች ክስተት መንስኤ፣ ሥርጭትና የጉዳት መጠን ስታንዳርዱን በጠበቀ ላቦራቶሪ ምርመራ በማረጋገጥ የመከላከያና የመቆጣጠሪያ ስልቶችን በመጠቆም በክልላችን ብሎም በሀገራችን የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ጨምሮና የህብረተሰቡ ጤና ተጠብቆ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና ብሔራዊ ብልጽግና ሰፍኖ ማየት፡፡

18/05/2026
18/05/2026
📢 FMD important Tips Foot-and-Mouth Disease (FMD)is one of the most highly contagious diseases affecting cattle, goats, ...
26/04/2026

📢 FMD important Tips

Foot-and-Mouth Disease (FMD)is one of the most highly contagious diseases affecting cattle, goats, sheep, and pigs.

It spreads rapidly and can cause huge economic losses due to reduced milk, weight loss, and movement restrictions.

🦠 Cause
FMD is caused by a virus that spreads through:
• Direct contact with infected animals
• Airborne droplets (especially in cool weather)
• Contaminated equipment, boots, clothes, and vehicles
• Infected feed, water, or pasture
• Farm visitors moving between herds

⚠️ Common Signs in Cattle
• Sudden high fever (40–41°C) 🌡️
• Excessive drooling or salivation 🤤
• Blisters in the mouth, tongue, lips, and gums 👄
• Blisters between hooves and around the coronary band 🐾
• Lameness — animals reluctant to walk
• Sharp drop in milk production 🥛⬇️
• Loss of appetite and weight loss
• Calves may die suddenly due to heart complications

🔍 What Happens to the Blisters
• Small fluid-filled vesicles appear
• They rupture within 1–2 days
• Painful wounds remain
• Animals stop eating or walking due to pain

🚨 Why FMD is Dangerous
• Spreads very fast within a herd
• Can infect multiple species on the farm
• Severe milk production losses
• Slow recovery affecting growth
• Trade and animal movement restrictions

🛡️ Prevention & Control Measures
✔️ Isolate infected animals immediately
✔️ Stop animal movement in and out of the farm 🚧
✔️ Disinfect boots, equipment, and vehicles 🧴
✔️ Restrict visitors
✔️ Use farm-specific clothing
✔️ Vaccinate where vaccines are available 💉
✔️ Dispose of contaminated materials properly
✔️ Clean and disinfect sheds regularly

💊 Treatment
There is no specific cure for the virus, but supportive care helps:
• Provide soft feeds (hay, mash) 🌾
• Give plenty of clean water 💧
• Clean mouth and foot wounds
• Use antiseptics for sores
• Veterinarian may give antibiotics to prevent secondary infections

📢 Important Tip for Farmers
Early detection and quick isolation is the best way to stop the spread. If you see drooling and lameness together, suspect FMD and act immediately.

ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሰን !!
10/04/2026

ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሰን !!

24/03/2026
የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች በተለይም ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ወቅታዊ ከመሆኑ አኳያ እጅግ የሚበረታታና ሊቀጥል የሚገባ ነው። ቢሯችን ለሰጠው ልዩ ትኩረት በጣም እናመ...
22/03/2026

የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች በተለይም ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ወቅታዊ ከመሆኑ አኳያ እጅግ የሚበረታታና ሊቀጥል የሚገባ ነው።
ቢሯችን ለሰጠው ልዩ ትኩረት በጣም እናመሰግናለን።

ኢድ ሙባረክ!ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447 ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ታላቁ ረመዷን የደስታ የፍቅር የጤናና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መ/ቤታ...
19/03/2026

ኢድ ሙባረክ!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447 ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ታላቁ ረመዷን የደስታ የፍቅር የጤናና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መ/ቤታችን መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

የሶዶ ክልላዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ላቦራቶሪ ማዕከል
ወላይታ ሶዶ; መጋቢት 11, 2018 ዓ.ም

19/03/2026

ከክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ የዒድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ የተላለፈ መልዕክት ‼️

መላ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447 ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን❗️

.

የፆመ ረመዳን ወቅት አለፈ፤ ንፁህ ልቦች ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ፤ 1447 ኛው ኢዒ አል-ፈጥርም ተበሠረ❗️

የመከባበር እና የመቻቻል አብነት በሆነችው ሀገራችን በፆምና በፀሎት ከፈጣሪ ጋር የንስሀ ጊዜ ላሳለፋችሁ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን በዓሉ የእዝነት፣ የፍቅር፣ የስኬት እና የብልፅግና እንዲሆንልን እመኛለሁ‼️

ዒድ አል-ፈጥር ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው፤ ረመዳን ፍቅር ነው፤ ረመዳን ራሂመት ነው❗️

ስለሆነም መላ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዕሴታችሁንና ሰው ተኮር የመተጋገዝ አስተምህሯችሁን ጠብቃችሁ በዓሉን ከአቅመ-ደካሞች ጋር በአንድነት ማዕድ በማጋራት፣ የታረዙትን በማልበስ፣ ያዘኑትን በማፅናናት የማክበር የሁልጊዜ ልማዳችሁን እያስታወስኳችሁ እንኳን ለ1447 ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እላለሁ ‼️

በድጋሚ መልካም ዒድ አል-ፈጥር❗️

ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ
በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ

የእንስሳት በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ክትባት (Prophylaxis & Control)የአለም አቀፉ የእንስሳት ጤና ተቋም (World Organization of Animal Health /WOAH) ...
19/03/2026

የእንስሳት በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ክትባት (Prophylaxis & Control)

የአለም አቀፉ የእንስሳት ጤና ተቋም (World Organization of Animal Health /WOAH) ጥናት መሰረት ከ15 መዘርዝር ሀ (List A) ተብለው ከሚታወቁት በሽታዎች መካከል ስምንቱ (8) በክልላችን ብሎም በሀገራችን በርካታ አካባቢዎች ተንሰራፍተዉ የሚገኙ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ 72 መዘርዝር ለ (List B) ተብለዉ ከተለዩት በሽታዎች 20 ያክሉ እንደሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በሽታ የመከላከል ስራ በሽታን ከመቆጣጠር የበለጠ ተመራጭነት አለው፡፡

የእንስሳት በሽታ መከላከል (Prevention/prophylaxis) ማለት አንድን የእንስሳት በሽታ እንዳይከሰት አስቀድሞ የተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን በሽታ መቆጣጠር (Control) ደግሞ በሽታዎች ከተከሰቱ በኋላ የሚያደርሱትን ጉዳት (ህመምና ሞት) መቀነስና በሽታው ወደ ጤነኞቹ እንስሳት እንዳይዛመት ማገት ማለት ነው::

ድንበር-ዘለል የእንስሳት በሽታዎች ካላቸው ዓለም-ዓቀፋዊ ገፅታና ተዛማችነት አኳያ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡ እነዚህ በሽታዎች ባላቸው ፈጣን የተዛማችነት ባህርይ ምክንያት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉንም አካባቢዎች ሊያዳርሱና ወደ ጎረቤት ሃገራትና ክልሎች ሊዛመቱ ስለሚችሉ የበሽታ መከሰቻ ወቅት (Disease Calander) በመለየት እና የክትባት መስጫ ጊዜ ሰሌዳ (Vaccination calander)በማዘጋጀት በሽታዎቹን የመከላከልና የመቆጣጠሩ ተግባር ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡

ክትባት በሽታ ከመምጣቱ ወይም ከመከሰቱ በፊት ለመከላከል የሚሰጥ ሲሆን የእንሰሳት ጤና አጠባበቅ ዋነኛው ክፍል ነው፡፡ በክትባት ለመከላከል ለሚቻልባቸው በሽታዎች የክትባት መርሃ ግብር አውጥቶ መተግበር በሽታው ጉዳት ሳያደርስ መከላከል ስለሆነ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ክትባት በሚሰጥበት ወቅት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች;

• የእንስሳቱ አይነትና ዝርያ፣- የሀገረሰብ እና የውጭ ሀገር የደም ዝርያ ያላቸዉ እንስሳት፣ ዳልጋ፣ አነስተኛ አመንዣኪ፣ ጋማ፣ ውሻና ድመት ወይም ሌሎችን መለየት፤

• የዕድሜ ገደብ፣- የእድሜ ገደባቸዉ ከ1 ወር በታች ፣ ከ 1-6 ወር እና ከ 6 ወር በላይ እየተለዩ የክትባት አምራቹ በሚያዘው መመሪያ መሰረት መስጠት፤

• የሚገኙበት ስነ-ህይወታዊ ሁኔታ ፡- ጊደር፣ እርጉዝ፣ የምትታለብ፣ የነጠፈች መሆናቸውን ማረጋገጥ፤

የክትባት ውጤታማነትን ሊወስኑ የሚችሉ እና መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፡

=> ክትባቱ የሙያዉ ባለቤትና ተጠያቂ በሆኑ ሰዎች/ባለሙያ ብቻ ይሰጣል፤

=> የክትባት መስጫ ሲሪንጅና መርፌ ጫፎች ለ15 ደቂቃ ያህል መቀቀል ይኖርባቸዋል፣

=> ክትባት በሚሰጥበት ወቅት የክትባት መርፌ ጫፎች ያልተጣመሙና ያልዶለዶሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያሻል፣

=> ለክትባቱ የሚያስፈልገውን የቅዝቃዜ መጠንና ሰንሰለት መጠበቅ ይገባል፣

=> የቅዝቃዜ ሰንሰለት መጠበቅ ያለባቸው ክትባቶች በረዶ ከቀለጠ በኋላ ወደ ፍሪጅ መመለስ አለባቸው እንጅ መሰጠት የለበትም፤

=> ክትባቱን ከመስጠት በፊት በደንብ ማዋሀድ ያስፈልጋል፤

=> ጤነኛ እንስሳት ብቻ መከተብ ይኖርባቸዋል፤

=> የትኛውም የእንስሳት በሽታ መከላከያ ክትባት ለሙቀትና ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ የለበትም፣

=> በቆዳ ስር በሚሰጥ የክትባት (Subcutaneous injections /Sc ), በስጋ ውስጥ (Intramuscular/Im) መስጠት የተከለከለ ነዉ (ከዶሮ ውጪ)፤

=> ለእርጉዝ እንስሳት የሚሰጥ ክትባት ህይወት የለለው መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤

=> በሁለት ሳምንት ውስጥ ለእርድ ለሚቀርቡ እንስሳት ክትባት አይሰጥም፤

=> በመርፌ የሚሰጥ ህክምና ክትባቱ ከመሰጠቱ ቢያንስ ከ10 ቀን በፊት እና በኋላ መሰጠት የለበትም፡፡

=> አንዳንድ ክትባት አልፎ አልፎ ክትባቱ በተሰጠበት አካባቢ የሚታይ የማበጥ ምልክት ሊኖር ይችላል፡፡ እብጠቱ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ካልመጣ በቴትራሳይክሊን፣ ኦክሲቴትራሳይክሊን ወይም በኢርትሮማይሲን እንስሳቱን ማከም ያስፈልጋል፡፡ እብጠቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመጣ በታይሎሲን ማከም ያስፈልጋል፡፡

=> ክትባቱ ከተሰጠ በ2 ሳምንታት ዉስጥ እንስሳቱ ከበሽታ የመከላከል አቅማቸዉ ይጎለብታል፤

=> የክትባቱ በሽታ የመከላከያ ጊዜ በመያዣ ዕቃው ተለጥፎ ይገኛል፤ የተላጠ ወይም ማንኛውም መረጃ ብልቃጡ ላይ ከለለ ክትባቱ መሰጠት የለበትም፤

=> የተበጠበጠ ወይም የተከፈተ የመከላከያ ክትባት ከአንድ ሰዓት በላይ መቆየት የለበትም ወይም ተከፍቶ ከ3 ሰዓት በላይ የቆየ ክትባት መወገድ (Discareded) አለበት (Shelf life)፤

=> የእንስሳት በሽታ መከላከያ ክትባቶች ስራ ላይ ከመዋላቸው በፊት የተመረቱበት ቀን (Manufacturing date)፣ የመለያ ቁጥራቸው (Batch number) እንዲሁም የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸውን (Expiry date) የተመለከቱ መረጃዎች ክትባቱን በሚሰጠው የእንስሳት ጤና ባለሙያ በክሊኒኩ ውስጥ በሚገኝ መዝገብ ላይ በአግባቡ መስፈር ይገባል፡፡

«««ቃል በተግባር»»»ለዘመናት ደን ሆኖ የቆየው የማእከላችን ቅጥር ግቢ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በቢሯችን ም/ኃላፊና የእንስሳት ጤናና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ አስተባባሪ በሆኑት በዶ/ር አድ...
28/08/2024

«««ቃል በተግባር»»»
ለዘመናት ደን ሆኖ የቆየው የማእከላችን ቅጥር ግቢ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በቢሯችን ም/ኃላፊና የእንስሳት ጤናና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ አስተባባሪ በሆኑት በዶ/ር አድሱ ኢዮብ ሀ ተብሎ ላውንች በማድረግ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ልማት በወቅቱ በብቸኝነት የተተከለችው የፓፓያ ምርጥ ዘር በ2ኛዋ ዓመት ዕድሜ ዛሬ ላይ የ2ኛ ዙር ምርት በመስጠት ላይ የምትገኝ ሲሆን ከአንዲት ተክል በአንድ ጊዜ ብቻ ከ30 ፍሬ በላይ ፓፓዬ መልቀም እየተቻለ ነው።

እንደዚሁም በኢንሸቲቩ የተቀጣጠለው የግቢያችን ኮርደር ልማት የተለያዩ የፍራፍሬና የጓሮ አትክልት ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ የሆንንበት ተሞክሮ በሁሉም ተቋማትና በግለሰብ ማሳዎች በስፋት ማልማት ከተቻለ እንደ ሀገር የታለመለትን የሌማት ትሩፋት በቅርቡ እውን ከማድረግ የሚገዳደር ኃይል አይኖርም ።

ፈጣሪ የአየር ንብረቱን ጤና ከጠበቀ የሌማታችንን በረከት ከማሳችን እናረጋግጣለን!!

Address

Wolayta
Sodo
4620

Telephone

+46551259378

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo Regional Veterinary Laboratory posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category