Haramaya University

Haramaya University Haramaya University is one of the oldest universities in Ethiopia. It is located 5 km from Haramaya, welcome
(1)

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች ሐረማያ ሃይቅ ላይ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረማያ ሃይቅ ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዲኔ ረሺድ እንደገለጹ...
27/10/2025

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች ሐረማያ ሃይቅ ላይ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረማያ ሃይቅ ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዲኔ ረሺድ እንደገለጹት ሃይቁን ከቆሻሻ ለማጽዳት በየጊዜው መሰል የጽዳት ዘመቻዎች መካሄዳቸው እና ቅዳሜ የተከናወነው ዘመቻም በጎርፍ አማካኝነት በሃይቁ ዳርቻዎች የተከማቹ ጠጣር ቆሻሻዎችን ለማጽዳትና ሃይቁን ንጹህ በማድረግ በውስጡ ያሉ ስነ-ሕይወቶችን ደህንነት ለማስጠበቅ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሐይቁ ተፋሰስ ላይ ከሚያደርገው የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጎን ለጎን የሐይቁን ንጽህና ለማስጠበቅ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝና ለዚህ ስኬት በሐይቁ አከባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችም የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ አቶ ዲኔ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የማያ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልይ አብራሂም እንደገለጹት የሐረማያ ሃይቅን መንከባከብ የማንኛውም ማህበረሰብ የዜግነት ግዴታ መሆኑንና በጎርፍና በሌሎች መንገዶች ወደ ሃይቁ የሚገባው ቆሻሻ የሃይቁን ብዝሃ ህይወት ስለሚያዛባ በተቻለ መጠን ንጽህናው የተጠበቀ እንዲሆን ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኒቨርሲቲው ለሃይቁ እንክብካቤ የሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን አውስተው እንደ ማያ ከተማም በሳምንት አንድ ጊዜ በቋሚነት የሚጸዳበትን ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሃይቁን ለማጽዳት የሚያደርጉት ጥረት የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አቶ አልይ አክለው ገልጸዋል፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የክበባት አደረጃጀቶች ቦርድ ሰብሳቢ ተማሪ ሚደቅሳ ደጀኔ እንደገለጸው ይህንን የጽዳት ዘመቻ ከፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን በዋናነት የማህበረሰብ አገልግሎትና የአከባቢ ጥበቃ ክባባት ያስተባበሩ ሲሆን ሌሎች ክበባትና አደረጃጀቶችም መሳተፋቸውንና ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን መሰል የማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ተግባራዊ ልምድ የሚገኝበት ነው ብሏል፡፡

በጽዳት ዘመቻው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች እንዳሉት በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውንና በተለይ ሃይቁ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት የተፈጠሮ ሃብት በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ በየኔነት ስሜት ሊንከባከበው እንደሚገባ ተማሪ ኢሳያስ ሐይሉ ፣ ተማሪ ሐዊ አህመድና ተማሪ አብዱረዛቅ አወል ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አወቀ አያልነህ
ምስል፡ አሸናፊ ከበደና አወቀ አያልነህ

27/10/2025
የዓይን ሞራ ግርዶሽ ችግር ላለባቸው ህሙማን የነፃ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ዘመቻ በሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተሰጠየሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከፍሪድ ሐሎውስ ፋውንዴሽን እና ከ...
27/10/2025

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ችግር ላለባቸው ህሙማን የነፃ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ዘመቻ በሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተሰጠ

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከፍሪድ ሐሎውስ ፋውንዴሽን እና ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በአይን ሞራ ግርዶሽ ለሚቸገሩ ከምስራቅ ሀረርጌ ፣ ከድሬደዋ እና ከሀረሪ ክልል ለመጡ 1000 ታካሚዎች ለሰባት ቀናት የሚቆይ የነፃ ቀዶ ህክምና (የዓይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ) በመሰጠት ላይ ነው፡፡

የቀዶ ህክምናው አገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑት ታካሚዎችም የአይን ሞራ ግርዶሹ ካጋጠማቸው ጊዜ ጀምሮ በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው እና ይህን እድል በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኩል አግኝተው በመታከማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ዘመቻው በዋናነት በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በስፋት እየተስተዋለ ያለውን የአይን ሞራ ግርዶሽ ችግር ለመግታት ታስቦ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቀዶ ህክምና ዘመቻው የመጀመሪያ ቀን 150 ታካሚዎች አገልግሎቱን ያገኙ መሆናቸውንና በቀጣይ እስከ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም ሌሎች የዐይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ዘጋቢ፡- ታደለ ጥላሁን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርጥ ዘር የምርምር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማውጣት ማህበረሰቡንና አርሶ አደሩን እየጠቀመ ነው ተባለ በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ እና በምስራቅ ሐረርጌ ቀርሳ ወረዳ በሚገኙ የም...
27/10/2025

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርጥ ዘር የምርምር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማውጣት ማህበረሰቡንና አርሶ አደሩን እየጠቀመ ነው ተባለ

በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ እና በምስራቅ ሐረርጌ ቀርሳ ወረዳ በሚገኙ የምርምር ጣቢያዎች እንዲሁም በአርሶ አደሮች ማሳዎች ላይ የተሰሩ የእህልና የድንች ምርጥ ዘር የምርምር ስራዎች በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ፣ የግብርና ባለሙያዎች ፣ አርሶ አደሮች እና ዘር አምራች ማህበራት ተጎብኝተዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ከማል ቃሲም እንዳብራሩት ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ በምርምር ጣቢያዎች በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ስንዴ ፣ በቆሎ ፣ ማሽላ ፣ ጤፍ ፣ አተር ፣ ባቄላ ፣ ድንችና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ ከ67 በላይ ዝርያ ያላቸው የምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ ሰርቶ በማሳየት ፣ በማባዛት ፣ በማስተማር ፣ በማከፋፈልና ዘር አባዝተው የሚያከፋፍሉ ማህበራትን በመደገፍ አርሶ አደሩንና ማህበረሰቡን እየደገፈ መሆኑን አብራርተዋል።

የሃጃ ፈጅ የህብረት ስራ ማህበር ተወካይ እንዳሉት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በየጊዜው በምርምር የሚያወጣቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመውሰድ በአርሶ አደሩ የተመረጡ ዝርያዎችን አባዝተው በመሸጥ ተጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ አክሊሉ ሽፈራው በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ድርቅን የሚቋቋሙ ምርጥ ዘሮችን እያባዛ ለአርሶ አደሮች እንደሚሰጥና በዘንድሮ ዓመት የተፈጠረውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ የተከሰተውን የዘር እጥረት ክልሉ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ በመሆን መቅረፍ ተችሏል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ሐብታሙ ሐብተጊዮርጊስ
ፎቶግራፈር፡- በሀይሉ ግርማ እና ቴዎድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሪክቶሬት ዳይሪክተር
ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም

25/10/2025

A Warm Welcome from Haramaya University Student's Union!

Dear All 2018 Freshman Students,
On behalf of the Haramaya University Student’s Union, we extend a warm and heartfelt welcome to you!

To ensure your smooth arrival and transition, we have dedicated union members ready to assist you in Addis Ababa (Finfinne) and Adama.

Please feel free to contact them for any information, guidance, or assistance you may need. They are ready to help you.

Contact List for Assistance

Tamirat Gosa: 0941212654
Oliyad Ayano: 0926023260

(Finfinne)
Sifan Geremu: 0910571262
Jalene Fufi: 0951101263
Afendi Kemal: 0993302961

(Babur Station)
Hamden Jeylan 0982032722

We look forward to meeting you on campus and wish you all the best as you begin your academic journey!

Sincerely,
Haramaya University Student’s Union

የፈጠራ ፣ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ፣ ሽልማትና የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን ለመምራት የተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ውይይት ተካሄደየሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የስራ ፈጠራና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ዳይሬክ...
25/10/2025

የፈጠራ ፣ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ፣ ሽልማትና የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን ለመምራት የተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የስራ ፈጠራና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ዳይሬክቶሬት የፈጠራና ቢዝነስ ሃሳብ ውድድርን፣ ሽልማትንና የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን በተቋሙ ውስጥ ለመምራት የተዘጋጁ ረቂቅ ፖሊሲዎች ላይ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አባላትና ከተመራማሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ከማል ቃሲም እንደገለጹት የመመሪያዎቹ መዘጋጀት በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገቢ ምንጭነት ለመቀየር ፣ ተመራማሪው ተጠቃሚ እንዲሆንና በአጠቃላይ ስራው ተቋማዊ ይዘት ኖሮት በወጥነት እንዲመራ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የስራ ፈጠራና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ቅድስና ሰብስቤ በበኩላቸው ተመራማሪውና የስራ ፈጠራ ባለቤቱ መመሪያውን ተረድቶ ለውድድር እንዲቅርብና የልፋቱንም እንዲያገኝ የሚረዳ መሆኑንና የምርምር ውጤቶችም ወደ ታችኛው የማህበረሰብ ክፍል ደርሶ ችግር እንዲፈታ ያስችላል ብለዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተዘጋጀው መመሪያና አሰራር ላይ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በመመሪያው መሰረት በመስራት ከሚገኘው ገቢ ራሳቸውንም ተቋሙን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፦ አወቀ አያልነህ
ፎቶግራፈር፦ ፎአድ አህመድና በሀይሉ ግርማ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝን ለማሻሸል የተዘረጋው አሰራርን በተመለከተ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ካውንስል አባላት ገለፃ ተደረገ"HEMIS" የሚባለውን የመረጃ አያያዝና ...
25/10/2025

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝን ለማሻሸል የተዘረጋው አሰራርን በተመለከተ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ካውንስል አባላት ገለፃ ተደረገ

"HEMIS" የሚባለውን የመረጃ አያያዝና አሰራርን በተመለከተ ነው ገለጻ የተደረገው።

የዩኒቨርሲቲውን ሙሉ መረጃ በ"HEMIS" ሲስተም ውስጥ ገብቶ ለሚፈለገው ተግባር ይውል ዘንድ ሁሉም የስራ ክፍል ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ለተግባራዊነቱ ሊተጋ ይገባል ሲሉ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የሚኖረው ግንኙነትና ለዩኒቨርሲቲው የሚደረጉ ድጋፎችና ውሳኔዎች ሁሉ ከዚህ ሲስተም በሚገኝ መረጃ አማካኝነት ስለሚሆን ሁሉም የስራ ክፍል መረጃዎችን በማቅረብ ፣ በመከታተልና ትክክለኛነቱን በማጣራት የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ ስስተም ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን ሁሉም ዲኖች በሚሰጣቸው የመገልገያ ስምና የይለፍ ቃል በመግባት ማግኘት፣ ማየትና የተሞላው መረጃ ትክክለኛ መሆኑን ማጣራት እንደሚቻል በመድረኩ ላይ ስለ አሰራሩ ማብራሪያ ያቀረቡት ባለሙያዎች ገልጸዋል።

አሰራሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ስለ ዩኒቨርሲቲው ሙሉ መረጃ በማቅረብ ለበጀት አመዳደብ ፣ የዩኒቨርሲቲውን ደረጃ ለማውጣትና የተለያዩ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ እንደሚሆን ተገልጿል።

የ"HEMIS" ሲስተምን ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚጠቀሙበት እንደሆነና ሲስተሙን ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድረው መሆኑን በመድረኩ ላይ ከተሰጠው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ዘጋቢ፦ አወቀ አያልነህ
ፎቶግራፈር፦ ፎአድ አህመድና በሀይሉ ግርማ

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሮችን ቀን የግብርና ምርምር ውጤቶችን የመስክ ጉብኝት በማካሄድ ማክበር ጀመረ ትናንት በተጀመረው የመስክ ጉብኝት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣ የግብርና ባለሙያዎች ...
25/10/2025

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሮችን ቀን የግብርና ምርምር ውጤቶችን የመስክ ጉብኝት በማካሄድ ማክበር ጀመረ

ትናንት በተጀመረው የመስክ ጉብኝት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣ የግብርና ባለሙያዎች ፣ ተመራማሪዎች ፣ የማያ ከተማ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

በትናንትናው ዕለት የኢፋ ኦሮሚያ የቴክኖሎጂ መንደርን ፣ በኢፋ ባቴ ሞዴል አርሶ አደር መሬት ላይና በዩኒቨርሲቲው ራሬ የምርምር ማሳ ላይ የተሰሩ የምርምር ስራዎችን ተጎብኝተዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዲ መሐመድ እንደገለፁት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች በምርምር የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን በመስጠት ፣ በማሰልጠን በመደገፍ ፣ በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በተግባር በማሳየት የአርሶ አደሮችን ህይወት ለመለወጥ እየሰራ መሆኑ በመስክ ምልከታው የታዩት የስራ ውጤቶች ማሳያ ናቸው ተብለዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ከማል ቃሲም እንዳብራሩት የመስክ ምልከታው ዋና አላማ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ጣቢያዎችና በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ ላይ እየሰራ ያለውን የምርምር ፣ የኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመጎብኘት ውጤታማ መሆናቸውን ለማረጋገጥና ልምድ ለመለዋወጥ ነው ብለዋል።

አቶ ከማል አክለውም የምርምር ውጤቶች በኤክስቴንሽን አገልግሎት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ቢሆኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማህበረሰቡና ለግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ የመስክ ጉብኝቱ ማሳያ ይሆናል ብለዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የምርምር ውጤት የሆኑ ምርጥ ዘሮችን በመስጠት ፣ በማሰልጠንና የስንዴ ምርት በአካባቢው እንዲስፋፋ በማድረግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ያሉት የማያ ከተማ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ናቸው።

ተሳታፊ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማሳቸው ድረስ በመምጣት ጭምር ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውና ካዩት የምርምር ውጤቶችም ልምድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ።

የመስክ ጉብኝቱ ዛሬ ቀርሳ ወረዳ እየተካሄደ ሲሆን ሰኞ ዕለት ደግሞ ሂርና ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕከል ውስጥ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሀ ግብር ታውቋል።

ዘጋቢ ፦ ሐብታሙ ኃ/ጊዮርጊስ
ፎቶግራፈር፦ በሀይሉ ግርማ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 15 ቀን 2018ዐ ዓ/ም

Address

Haramaya
Bate
138

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haramaya University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Haramaya University:

Share

Our Story

Well Come To Haramaya University Official page

Historical Background of the University Haramaya University has gone through a series of transformations since its establishment as a higher learning institution. The agreement signed between the Imperial Ethiopian Government and the Government of the United States of America on May 15,1952 laid the foundations for the establishment of Jimma Agricultural and Technical School and the Imperial College of Agricultural and Mechanical Arts (IECAMA). The Agreement between the Government of Ethiopia and the Technical Cooperation Administration of the Government of the United States of America, signed on May 16, 1952, gave the mandate to Oklahoma State University to establish and operate the College, conduct a nationwide system of Agricultural Extension and set up an agricultural research and experimental station. Based on the Emperor’s wish, it was decided to establish the College at its current location at Haramaya. Later on, the agreement signed between the United States Department of States and the Imperial Government provided the basis for the operation of Jimma Agricultural and Technical School that received its first class of eighty students in October 1952. Nineteen of the students graduated on August 6, 1953 and became the first freshman students of the Imperial Ethiopian College of Agricultural and Mechanical Arts (IECAMA). The IECAMA opened its doors to its first batch of students in October 1956 senior class moved from Addis Ababa to Alemaya for their final semester. At the end of the 1956/57 academic year, eleven students completed their studies and graduated with a B.Sc. degree in General Agriculture. The training programs in Agriculture were further specialized and B.Sc. programs were introduced in Animal Sciences (1960), Plant Sciences (1960), Agricultural Engineering (1961) and Agricultural Economics (1962). Until 1963, the college was virtually dependent on Oklahoma State University, both administratively and academically; however, after 1966, when the first Ethiopian dean was appointed, the role of Americans was limited to advisory and technical support. The College became a chartered member of Addis Ababa University (the then Haile Selassie I University), following the contractual termination of Oklahoma State University in 1968. Consequently, it was named Alemaya College of Agriculture. Due to the great need of trained manpower in other areas of study, additional programs that included a diploma program in Home Economics (1967), Science Teachers’ Training Program (1978), and Continuing Education Program (1980) were launched. A major landmark in the history of the College of Agriculture was the launching of graduate study programs in the 1979/80 academic year. This laid the foundation for advanced academic and research work at the institution. When graduate studies were launched, about 29 students were enrolled to study various fields of agriculture. Another major landmark in the history of Alemaya College of Agriculture was when it was upgraded to university status on May 27, 1985, followed by the launching of the Faculty of Forestry in 1987. It was then named Alemaya University of Agriculture that produced qualified manpower in the fields of Animal Sciences, Plant Sciences, Agricultural Economics, Agricultural Engineering, Agricultural Extension and Forestry both at graduate and undergraduate levels. Moreover, in the continuing education program, diploma level training programs were delivered in Accounting and Management, in Dire Dawa and Harar centers. The university once again went through another phase of transformation during the 1995/96 academic year by launching new programs in the fields of Teacher Education and Health. The opening of the two faculties, namely the Faculty of Education and the Faculty of Health Sciences, further diversified the existing programs, and enabled the institution to become a full-fledged university that was renamed Alemaya University (AU). In the last few years, the University has witnessed tremendous expansion in terms of fields of study. In September 2002, two more faculties, namely Faculty of Law and Faculty of Business and Economics, were opened. Furthermore,Faculty of Veterinary Medicine and Faculty of Technology were initiated in 2003 and 2004, respectively to further diversify the training programs of the university. The institution was renamed Haramaya University in February 2006. The University, apart from undergraduate programs, has been highly engaged in the expansion and diversification of graduate programs. .....