Volunteer Vet.Care

Volunteer Vet.Care ለእንስሳትዎ ፍቅር እና እንክብካቤ!
🩺 የጤና መረጃዎችና የህክምና ምክሮች
የእርባታና የዝርያ ማሻሻል ስልቶች
🐂 እንዲሁም ለድለባ አገልግሎት ጠቃሚ ምክሮች
📲 ቴሌግራም፦
Gmail፦[email protected]

በየመስኩ በየሜዳው ለሀገራችን እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ እንዲሁም የአርሶና አርብቶአደሮቻችን የኑሮ ማገር የሆነውን ሀብቱን ለመጠበቅ ደፋ ቀና የሚሉ ያልተዘመረላቸው አርበኞቻችን። የላቀ ክብር ይገ...
06/06/2026

በየመስኩ በየሜዳው ለሀገራችን እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ እንዲሁም የአርሶና አርብቶአደሮቻችን የኑሮ ማገር የሆነውን ሀብቱን ለመጠበቅ ደፋ ቀና የሚሉ ያልተዘመረላቸው አርበኞቻችን። የላቀ ክብር ይገባቸዋል።

Big shout out to my newest top fans! Amare Muluneh Aml San Nigusie Mohammed Sulamo Awol Tibeyin Tewachew Jack Negn Ye Paul Belete Mossie Abitew Akalu Ambi Sikima Demissie Adamu Abera Omer Hussen WT ZT Menzir Awoke Zeynedin Ali GEbrie Eshetie Mulleta Kubi ሞገስ አበበ Ijolo Wariday Lamme Abdisa Oshonu Roba Sultan Nasir Abu Muaz Yihun Esubalew

ባክቴሪያውን ገደልን ግን ፍየሏ መሞቷ አልቀረም! የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በዚህ ላይ ምን ትላላችሁ?ብዙ ጊዜ የቤት እንስሳት በከባድ ተላላፊ በሽታ በተለይ ደግሞ በሳንባ በሽታ ወይም በሲሲፒ...
06/06/2026

ባክቴሪያውን ገደልን ግን ፍየሏ መሞቷ አልቀረም! የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በዚህ ላይ ምን ትላላችሁ?

ብዙ ጊዜ የቤት እንስሳት በከባድ ተላላፊ በሽታ በተለይ ደግሞ በሳንባ በሽታ ወይም በሲሲፒፒ (CCPP) ሲያዙ በቀጥታ ወደ ጠንካራ አንቲባዮቲክስ እንደ ታይሎሲን ወይም ኦክሲቴትራሳይክሊን መሮጥ የተለመደ ነው። ነገር ግን በሕክምና ሂደት ውስጥ ብዙ ጊዜ የምንዘነጋው አንድ ትልቅ ምስጢር አለ።

አንቲባዮቲኩ በሰውነት ውስጥ ያሉትን ባክቴሪያዎች አድኖ ለመግደል የተወሰነ ጊዜ ይፈጅበታል። ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ግን እንስሳው በከፍተኛ ትኩሳት፣ በሳንባ እብጠት እና በኃይለኛ የህመም ስቃይ ምክንያት መተንፈስ አቅቶት ቀድሞ ሊሞት ይችላል። ባክቴሪያው በመድኃኒቱ ቢሞትም እንስሳውን ግን በከፍተኛ ህመም ምክንያት ልናጣው እንችላለን ማለት ነው።

እዚህ ጋ ነው እንግዲህ የኛ የባለሙያዎች ንቃተ ህሊና የሚመዘነው። በዚህ ሰዓት ሜሎክሲካም የተባለውን መድኃኒት በረዳትነት ወይም ለሰፓርቲቭ ቴራፒ አብሮ መውጋት በፍጹም መዘንጋት የለበትም።

ሜሎክሲካም ባክቴሪያ ባይገድልም ለአንቲባዮቲኩ ሥራ መሳካት ሜዳውን ያመቻቻል። አንደኛ ነገር ትኩሳቱን በፍጥነት በማውረድ እንስሳውን ከሞት ጫፍ ይመልሰዋል። ሁለተኛ በሳንባና በጡንቻዎች ላይ የሚፈጠረውን አስጨናቂ የውስጥ ብግነት ወይም እብጠት ያጠፋለታል። ሶስተኛውና ዋናው ነገር ደግሞ ህመሙ ስለሚቀንስለት እንስሳው ወዲያው ተነስቶ መጋጥና መብላት እንዲጀምር ያደርገዋል። ባጭሩ አንቲባዮቲኩ ዋናውን ጠላት ሲዋጋ ሜሎክሲካም ደግሞ ለእንስሳው ጊዜና የመኖር ዕድል ይገዛለታል።

ለአርቢዎችና ለእንስሳት ባለቤቶች የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ አለኝ። ይህ መረጃ ስለ መድኃኒቱ ሳይንሳዊ ጥቅም ለማስተማር ብቻ የተዘጋጀ ነው። የሜሎክሲካም መጠን ልኩ ካልተጠበቀ ወይም ከተገቢው አንቲባዮቲክ ጋር በባለሙያ ካልተቀናጀ በእንስሳቱ ላይ የኩላሊትና የጨጓራ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በመሆኑም እዚህ ጋ አነበብን ብላችሁ እንስሳቶቻችሁ ሲታመሙ በራሳችሁ ውሳኔ መድኃኒት ከመውጋት ተቆጠቡ። ይልቁኑ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የእንስሳት ጤና ተቋም ወይም ወደ ባለሙያ በመውሰድ አሳክሙ።

​ለመጨረሻ ያህል አንድ የውይይት ጥያቄ ላንሳ። በየክሊኒካችሁ ወይም በአካባቢያችሁ በሚገኙ የእንስሳት ሕክምና ጣቢያዎች ላይ አንቲባዮቲክን ከሜሎክሲካም ጋር አቀናጅቶ የመስጠት ልምድ ምን ይመስላል? ያያችሁትስ የፈውስ ልዩነት ምንድነው? ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩኝ።
​እውቀቱ ለሁሉም ባለሙያዎችና አርቢዎች እንዲደርስ ፖስቱን ሼር በማድረግ ተባበሩ።

#ሜሎክሲካም

🐑🐐 ከቦረና ምድር የተሰማው የምስራች፡ 135 ሺህ ለሚሆኑ በጎችና ፍየሎች የተደረገው ታላቅ ዘመቻ! በቦረና ዞን በሞያሌ ወረዳ የውጭ ጥገኛ ተውሳኮችን ለመከላከል የሚረዳ የኬሚካል መድኃኒት ር...
06/06/2026

🐑🐐 ከቦረና ምድር የተሰማው የምስራች፡ 135 ሺህ ለሚሆኑ በጎችና ፍየሎች የተደረገው ታላቅ ዘመቻ!

በቦረና ዞን በሞያሌ ወረዳ የውጭ ጥገኛ ተውሳኮችን ለመከላከል የሚረዳ የኬሚካል መድኃኒት ርጭት (የቢፍ ዘመቻ) ተጀመረ።

መንግሥት ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ምክንያት፣ የእንስሳቶቻቸው ጤንነት እየተጠበቀላቸውና ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን የሞያሌ ወረዳ አርብቶ አደሮች ገልጸዋል።

በዚህ ዘመቻ ላይ በበጎችና በፍየሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እንደ መዥገር ፣ ቁንጫ እና ሌሎች የውጭ ጥገኛ ተውሳኮችን ለመከላከል የመድኃኒት ርጭት መጀመሩን በቦረና ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት የእንስሳት ጤና ጥበቃ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ገልማ ዋቆ አስታውቀዋል።

ይህ የተጀመረው የኬሚካል መድኃኒት ርጭት የእንስሳቱን የቆዳና ሌጦ ጥራት ለመጠበቅ እንዲሁም ምርታማነታቸውን (ወተትና ስጋን) በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር እንደሚያግዝም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል።

​በዞኑ በአጠቃላይ ከ135,000 (አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ) በላይ በጎችና ፍየሎች የዚህ የውጭ ጥገኛ ተውሳክ መከላከያ መድኃኒት ርጭት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የቦረና ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ አስጨናቂ አስረድተዋል።

​💬 የእርስዎ አስተያየት፦ እንደ ቦረና ዞን ሁሉ በየአካባቢያችን ያሉ የመስክ ባለሙያዎች (ልክ በምስሉ ላይ እንደምናየው) አስቀድሞ የመከላከል ስራዎችን በሰፊው እንዲያዳርሱ ምን መደረግ አለበት ይላሉ? ሐሳባችሁን በኮሜንት አካፍሉን! 👇

#የእንስሳትጤና #የመከላከልዘመቻ #ቦረና #ሞያሌ #በጎችናፍየሎች

​ምንጭ፦ ‘OBN Cyber Media’ — ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

‎​📌 ከታሪክ ማህደር እስከ ዛሬው ስሌት (የቀድሞው ራዕይና የዛሬው እውነታ)‎                ክፍል አንድ‎ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የረራትን የእን...
06/06/2026

‎​📌 ከታሪክ ማህደር እስከ ዛሬው ስሌት (የቀድሞው ራዕይና የዛሬው እውነታ)

ክፍል አንድ

‎ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የረራትን የእንስሳት ሕክምና ትምህርት ቤት እና የከብት ሕክምና ኢንስቲትዩት ሲያስመርቁ ያደረጉትን ንግግርና የቆመለትን ታላቅ ዓላማ ስንመለከት፣ ዘርፉ ገና ድሮ ምን ያህል ትልቅ ብሔራዊ ትኩረት እንደተሰጠው እንረዳለን።

‎ንጉሠ ነገሥቱ በዘመኑ የነበራቸውን ብሩህ ራዕይ በንግግራቸው ላይ እንዲህ ገልጸውት ነበር፦

‎​“በዘመነ መንግሥታችን ኢትዮጵያ ካደረገቻቸው አንዱ የከብቶች ጤና ጥበቃ መቋቋም ሲሆን፤ ይህ ዛሬ መጋረጃውን የምንከፍተው የከብት ሕክምና ኢንስቲትዩትና የረራትን ሐኪሞች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ጠቃሚ እርምጃ ነው ብለን እናስባለን።”

‎ያኔ ከተጣለው መሠረት የምንማራቸው 3 ዋና ቁምነገሮች፦

‎1ኛ ​የተፈጥሮ ሀብትን በሳይንስ ማገዝ 🔬፦

‎ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አገር ብትሆንም፣ ይህንን ሀብት በዘፈቀደ ከመጠበቅ ባለፈ በሳይንሳዊ መንገድ ማሻሻል ለሀገር እድገት መሠረት እንደሚሆን ያኔ በጽኑ ይታመንበት ነበር።

‎2ኛ ​የእንስሳት እርባታ የኢኮኖሚው ዋስትና መሆኑ፦

‎የሀገራችንሕዝብ አብዛኛው በግብርናና በእርባታ የሚተዳደር እንደመሆኑ መጠን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓለምን እየቀየሩ በነበሩበት በዚያ ዘመን የእንስሳትን ጤና በዘመናዊ መንገድ መጠበቅ የኢኮኖሚው ዋና ምሰሶ ተደርጎ ተወስዷል።

‎3ኛ የዘመናዊነት ጥሪ 🌍፦ ዘመኑ ከሚጠይቀው ስልጣኔ ጋር እኩል ለመራመድ እንስሳትን በጤናቸው፣ በአያያዛቸውና በጥቅማቸው ረገድ በጥንቃቄ መያዝ እና ማሻሻል እንዳለበት ያኔ የተጣለ ጽኑ መሠረት ነው።

‎ዛሬ ላይ የት መድረስ ነበረብን? (የስሌት እውነታው)
‎​ኢትዮጵያ በአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀስ ግዙፍ የእንስሳት ሀብት አላት። ገና በ1960ዎቹ የተጀመረው ዘመናዊ መሠረት ያንን ትኩረትና ቀጣይነት አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ፦

‎👉​ሀገራችን የወተት፣ የስጋና የቆዳ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በከፍተኛ ጥራት የምታቀርብ ዋና የወጪ ንግድ (Export) መናኸሪያ መሆን ነበረባት።

‎👉​በየቀበሌው ያሉ አርሶ አደሮች ሙሉ በሙሉ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ የእንስሳት ሕክምናና የክትባት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ነበረባቸው።

‎👉​የባለሙያዎቻችን ደህንነት ጥቅማጥቅምና የሥራ ላይ ቁሳቁስ አቅርቦት ደረጃውን የጠበቀ መሆን ነበረበት።

‎ነገር ግን ታሪካዊ መነሻችንን ዛሬ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ስናሰላው፣ ከነበረን እምቅ አቅምና ቀደምት ራዕይ አንጻር ዘርፉ እጅግ ወደኋላ የቀረና ብዙ መስተካከል ያለባቸው ድክመቶች ያሉበት ሆኖ እናገኘዋለን።

‎(በሚቀጥለው ክፍል ዋና ዋና ድክመቶቻችንን እና መፍትሔዎቻቸውን በዝርዝር እንመለከታለን ይቆዩን!)

ምስል፦ ከባልደረቦቻችን

#የእንስሳትሕክምናታሪክ #የኢትዮጵያታሪክ #የመስክባለሙያዎች #የእንስሳትጤና

የሆለታው ስልጠና እና የወተት ምርትን ለማሳደግ የተያዘው አዲስ ግብግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ምየእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት (ሆለታ)የአገር በቀል ላሞቻችንን ዝርያ በማሻሻል ረገድ የሚታየው...
05/06/2026

የሆለታው ስልጠና እና የወተት ምርትን ለማሳደግ የተያዘው አዲስ ግብ

ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት (ሆለታ)

የአገር በቀል ላሞቻችንን ዝርያ በማሻሻል ረገድ የሚታየውን የወተት እጥረት ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀው የ62ኛው ዙር የአዳቃይ ቴክኒሽያን የተግባር ስልጠና በሆለታ ማዕከል ተጠናክሮ ቀጥሏል።

​ኢንስቲትዩቱ በያዝነው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 600 የዘርፉን ባለሙያዎች ለማፍራት አቅዶ እየሰራ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 14 ሴቶችን ጨምሮ 138 ሰልጣኞች በዚህ ማጠቃለያ ዙር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የስልጠናው አስተባባሪና ተመራማሪ አቶ አምዴ መኮነን እንደገለጹት፣ ይሄኛው የልማት ስራ የአገር በቀል ላሞቻችንን ዝርያ ከፍተኛ ምርት ከሚሰጡ የውጭ ከብቶች ጋር በማዳቀል ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

​ለ45 ቀናት የተዘጋጀውን የንድፈ ሃሳብ ትምህርት ያጠናቀቁት እነዚህ ባለሙያዎች፣ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በሜዳ ላይ የተግባር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ። ስልጠናውን ሲያጠናቅቁም ወደየአካባቢያቸው ተመልሰው ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ቀልጣፋ የሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎት በመስጠት ምርታማነትን ለማሳደግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​💬 እናንተስ ምን ታስባላችሁ? በአካባቢያችሁ ያለው የሰው ሰራሽ ማዳቀል (AI) አገልግሎት አሰጣጥ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ነው? ያጋጠሙ ማነቆዎችስ አሉ? ሃሳባችሁን በኮመንት ያካፍሉን!

#ሰውሰራሽማዳቀል #የከብትእርባታ #ዘመናዊእርባታ #የእንስሳትልማት #ሆለታ #ኢትዮጵያ

🩺 የቤት እንስሳትን በቤት ውስጥ ለማከም ከመሞከራችን በፊት ማወቅ ያለብን 3 ወሳኝ ነገሮች!​ብዙ ጊዜ የእንስሳት አርቢዎች ከብቶቻቸው ወይም ሌሎች እንስሳቶቻቸው ሲታመሙባቸው ባለሙያ ከማማከር...
05/06/2026

🩺 የቤት እንስሳትን በቤት ውስጥ ለማከም ከመሞከራችን በፊት ማወቅ ያለብን 3 ወሳኝ ነገሮች!

​ብዙ ጊዜ የእንስሳት አርቢዎች ከብቶቻቸው ወይም ሌሎች እንስሳቶቻቸው ሲታመሙባቸው ባለሙያ ከማማከር ይልቅ በራሳቸው ግምት መድኃኒት የመስጠት ወይም በባህላዊ መንገድ የማከም ልማድ ይታያል። ነገር ግን ይህ ልምድ ከጥቅሙ ጉዳቱ በእጅጉ ያመዝናል።

ዛሬ እንደ ባለሙያ እያንዳንዱ አርሶ አደርና አርቢ ሊያውቃቸው የሚገቡ 3 ወሳኝ ነጥቦችን እናካፍላችኋለን፦

1. የተሳሳተ ምርመራ እና የሀሰት እፎይታ ❌
የበሽታ ምልክቶች ሊመሳሰሉ ይችላሉ። ለምሳሌ በአይን ላይ የሚወጣ ፈሳሽ ተራ የአይን መቅላት ሊመስል ይችላል ነገር ግን የውስጥ ጥገኛ ተውሳክ ወይም የቫይረስ ምልክት ሊሆን ይችላል። ያለ ባለሙያ ምርመራ መድኃኒት መግዛት በሽታውን ከማባባስ ባለፈ ለእንስሳቱ ህልፈት ምክንያት ይሆናል።

​2. የመድኃኒት መላመድ
አንቲባዮቲክስ ወይም የትል ማጥፊያ መድኃኒቶችን ያለ ባለሙያ እገዛና መመሪያ መስጠት ባክቴሪያዎችና ጥገኛ ተውሳኮች መድኃኒቱን እንዲላመዱ ያደርጋቸዋል። ይህ ሲሆን በሽታው በቀጣይ በማንኛውም መድኃኒት የማይድን አደገኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል።

​3. የደህንነት ጊዜ (Withdrawal Period) ጥሰት 🥛🥩
ማንኛውም እንስሳ መድኃኒት ከተሰጠው በኋላ መድኃኒቱ ከሰውነቱ ሙሉ በሙሉ እስኪወጣ ድረስ ወተቱን ወይም ስጋውን ለምግብነት መጠቀም የተከለከለ ነው። ይህንን ሳያውቁ ለሰው ልጅ መመገብ ለተለያዩ የጤና እክሎች ይዳርጋል።

የእኛ መልእክት፡
​ማንኛውንም የጤና እክል ሲያዩ ቀዳሚ ምርጫዎ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የእንስሳት ጤና ባለሙያን ማማከር ይሁን። የእንስሶቻችን ጤና እና ደህንነት የእኛም ስኬት ነው!

​💬 በእናንተ አካባቢ ከብቶች ሲታመሙ በብዛት ባለሙያ የመጥራት ልማድ አለ ወይስ በራስ መንገድ ማከም? ልምዳችሁን በኮመንት አጋሩን! 👇

​ #የእንስሳትጤና #የእንስሳትህክምና #የከብትእርባታ

👁️ የእንስሳት አይን ትል በሽታ (Thelaziasis)በምስሉ ላይ የምናየው በከብቶች አይን ላይ የሚከሰትና የአይን ትል በመባል የሚታወቅ አደገኛ የጥገኛ ተውሳክ በሽታ ነው።​  #ስርጭት፦ በ...
03/06/2026

👁️ የእንስሳት አይን ትል በሽታ (Thelaziasis)

በምስሉ ላይ የምናየው በከብቶች አይን ላይ የሚከሰትና የአይን ትል በመባል የሚታወቅ አደገኛ የጥገኛ ተውሳክ በሽታ ነው።

​ #ስርጭት፦ በሽታው የሚተላለፈው በዝንቦች አማካኝነት ሲሆን፣ ዝንቦቹ የአይን ፈሳሽ ለመምጠጥ ሲያርፉ የትሉን እጮች ከአንዱ እንስሳ ወደ ሌላው ያጋባሉ።

​⚠️ ምልክቶች፦
_​ከአይን ላይ ከመጠን ያለፈ እንባና ፈሳሽ መፍሰስ።
_​የአይን መቅላት፣ ማበጥና ማሳከክ።
_​ብርሃን መፍራትና ካልታከመ ሙሉ በሙሉ መታወር።

#መፍትሄ፦
አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ ለመጎርጎር መሞከር የለበትም። በአቅራቢያው ወደሚገኝ የእንስሳት ጤና ባለሙያ በመውሰድ እንደ Ivermectin ያሉ በትል ማጥፊያ መድኃኒቶች ፣በአይን ጠብታዎች ወይም ባለሙያው በጥንቃቄ ትሎቹን በእጅ እንዲያወጣቸው በማድረግ ማከም ይቻላል። በበረቶች አካባቢ የዝንብ ማጥፊያ በመጠቀም በሽታውን አስቀድሞ መከላከል ይመረጣል።

​💬 በእናንተ አካባቢ እንዲህ አይነት በሽታ ገጥሟችሁ ያውቃል? ሀሳባችሁን በኮመንት አጋሩን! 👇

​ #የእንስሳትጤና #የአይንትል #ኢትዮጵያ

በአርሲ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ አጥብቀን እንቃወማለን! ❌​የዜጎችን በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ማስከበር ያልቻለ መንግስት ህልውናው አጠያያቂ ነው። የንጹ...
03/06/2026

በአርሲ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ አጥብቀን እንቃወማለን! ❌

​የዜጎችን በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ማስከበር ያልቻለ መንግስት ህልውናው አጠያያቂ ነው። የንጹሃን ደም በየቦታው እየፈሰሰ ዝም ብሎ ማየትና ተገቢውን ጥበቃ አለማድረግ ታሪካዊ ተጠያቂነትን ያስከትላል።

የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ ኃላፊነቱን ይወጣ!! የዜጎች ህይወት ከርካሽ የፖለቲካ ትርፍ በላይ ክቡር ነው!

​ለተጎዱ ወገኖቻችን መፅናናትን፣ ለሀገራችን ሰላምን እንመኛለን። ፈጣሪ ግፈኞችን የእጃቸውን ይስጣቸው።

#አርሲ #ፍትህ

አርሶ አደር ወይም አርብቶ አደር አልያም የአርሶአርብቶ አደር ቤተሰብም ብትሆኑ   አንብቡት ታተርፉበታላችሁ!!የእንስሳትን ጤና ለመጠበቅና ምርታማነትን ለማሳደግ የክትባት ሚናበሀገራችን የኢኮኖ...
03/06/2026

አርሶ አደር ወይም አርብቶ አደር አልያም የአርሶአርብቶ አደር ቤተሰብም ብትሆኑ አንብቡት ታተርፉበታላችሁ!!

የእንስሳትን ጤና ለመጠበቅና ምርታማነትን ለማሳደግ የክትባት ሚና

በሀገራችን የኢኮኖሚ መሠረት በሆነው የግብርናው ዘርፍ ውስጥ የእንስሳት ሀብት ልማት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። ሆኖም ግን በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች በዘርፉ ላይ ትልቅ ተግዳሮት እየሆኑ ይገኛሉ። እንደ አንድ የእንስሳት ጤና ባለሙያ እነዚህን ተላላፊ ወረርሽኞች ለመቆጣጠር በሳይንስ የተረጋገጠውና ቀዳሚው መከላከያ ዘዴ የእንስሳት ክትባት መሆኑን በጽኑ ላስገነዝብ እወዳለሁ።

የእንስሳት ክትባት የሚከተሉት ሦስት ዋና ዋና ፋይዳዎች አሉት ፦

1ኛ ፦ እንደ የቆዳ ጉርብርብ/እብጠት በሽታ ያሉ በቫይረስ የሚመጡና በነፍሳት አማካኝነት በፍጥነት የሚሰራጩ በሽታዎችን አንዴ ከተከሰቱ በኋላ ለማከም አስቸጋሪ በመሆኑ በሽታው ሳይከሰት አስቀድሞ ማስከተብ ብቸኛው መፍትሄ ነው።

2ኛ ፦
ክትባት ከብቶች በህመም ምክንያት የሚገጥማቸውን የወተትና የሥጋ ምርት መቀነስ ያስቀራል። በተጨማሪም ድንገተኛ የከብቶች ሞትን በመግታት የእርስዎን የሀብት መሠረት በዘላቂነት ይጠብቃል።

3ኛ ፦
ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የክትባት ሚና ከፍተኛ ነው። ጤናማ እንስሳት ንጽህናው የተጠበቀ ምርት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ ያደርጋሉ።

​በመጨረሻም እንስሳትን ማስከተብ ወጪ ሳይሆን የነገውን ምርትና ገቢ ዋስትና የሚያረጋግጥ አስተማማኝ ኢንቨስትመንት መሆኑን ተገንዝበንምንጊዜም ከብቶቻችንን በወቅቱ እንድናስከትብ ሙያዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

#የእንስሳትጤና #የክትባትዘመቻ #የቆዳእብጠትበሽታ #ሀላባዞን

Photo Illustration Only

የእንስሳትን ጤና ለመጠበቅ ያለመ የL*D ክትባት ዘመቻ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በመካሄድ ላይ ነው።​የዕለቱ ዋና ዜናሀላባ ዞን፣ ዌራ ወረዳበሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የእንስሳትን ደህንነት ለመጠበ...
03/06/2026

የእንስሳትን ጤና ለመጠበቅ ያለመ የL*D ክትባት ዘመቻ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በመካሄድ ላይ ነው።
​የዕለቱ ዋና ዜና
ሀላባ ዞን፣ ዌራ ወረዳ

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የእንስሳትን ደህንነት ለመጠበቅ በበሽታዎች ምክንያት የሚከሰተውን የምርት መቀነስና የከብቶች ሞት ለመከላከል የታቀደው የLumpy Skin Disease (L*D) ወይም ተላላፊ የቆዳ ጉርብርብ በሽታ የክትባት ዘመቻ በስኬት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ይህ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣውና በትንኞች እንዲሁም በዝንቦች አማካኝነት በፍጥነት የሚሰራጨው የቆዳ እብጠት በሽታ በከብቶች ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በሽታው ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ብቸኛውና አስተማማኙ መፍትሄ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የአርሶ አደሩ ንቁ ተሳትፎ እና የባለሙያዎች ቁርጠኝነት
​የክትባት ዘመቻውን ሂደት አስመልክቶ ከተለያዩ የክትባት ጣቢያዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የአካባቢው አርሶ አደሮች የእንስሳት ጤናን ጥቅም በሚገባ በመገንዘብ ከብቶቻቸውን በነቂስ ወደ ክትባት ጣቢያዎች በማምጣት ላይ ይገኛሉ።

ዘመቻው ደረጃውን የጠበቀ እና ለእንስሳቱም ሆነ ለባለሙያዎቹ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ልዩ ጥንቃቄ እየተደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት ከብቶቹ ያለምንም መረባበሽ ክትባቱን እንዲያገኙ ለማድረግ የእንስሳት መያዣ አጥር (Crush) ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ተገልጿል።

የወረዳው የእንስሳት ጤና ጥበቃ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንደገለጹት የእንስሳት ጤና የህብረተሰቡ ጤና እና የሀገር ኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ ዘመቻው ተደራሽነቱን ያሰፋል ተብሏል። በመሆኑም እስካሁን ከብቶቻቸውን ያላስከተቡ የአካባቢው አርሶ አደሮች በሙሉ በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የክትባት ጣቢያዎች በመውሰድ የእንስሳት ሀብታቸውን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

ጥያቄ ለወዳጆቻችን??

በእርስዎ አካባቢስ የእንስሳት በሽታዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚደረጉ የክትባት ዘመቻዎች ተደራሽነት ምን ይመስላል? አርሶ አደሩን ይበልጥ ለማንቃትና የእንስሳት ጤና አገልግሎትን ለማዘመን ምን መደረግ አለበት ይላሉ? የእርስዎን ጠቃሚ ሃሳብና አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ ያካፍሉን።

​ #ሀላባዞን #ዌራወረዳ #የእንስሳትጤና #የክትባትዘመቻ #የቆዳእብጠትበሽታ *DVaccination

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Volunteer Vet.Care posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Volunteer Vet.Care:

Share

Category