Ethiopia Horse Riding

Ethiopia Horse Riding Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Horse Riding, Atlas, Addis Ababa.

07/05/2026
07/05/2026

㊙️በደርግ መንግሥት የደህንነት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደሥላሴ ስለ እነ ኃይሌ ፊዳ አሟሟት የተናገሩት
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
🔸ገነት - ኃይሌ ፊዳ፣ ዶክተር ንግሥት አዳነ እና ሌሎችም የራስ አሥራተ ካሣ መኖሪያ ቤት የነበረው ውስጥ ታስረው ቆይተው በኋላ በመገደላቸው ዐፅማቸው ተገኝቶ ወጥቷል፡፡ ማነው የገደላቸው? መንግሥቱ ኃይስማርያም «የተገደሉት በገበሬዎች ነው:: በቁጥጥር ሥር ውስጡ እንደነበር አላውቅም» ይሳሱ፡፡ እርስዎስ ስስዚህ የሚሉት አስ?

🔹ተስፋዬ - እሳቸው ሊክዱ ይችላሉ፡፡ እነኃይሌ ፊዳና ሌሎችም የፖለቲካ ካድሬዎች፣ በተለይም ፈርጣጭ መኢሶን የተባሉት ሁሉ የታሰሩት ደርግ ጽህፈት ቤት ነው፡፡ የተመረመሩት በደርግ መርማሪዎች ነው፡፡ እኛ ምንም ነገር ውስጥ የለንበትም፡፡

🔸ገነት- እናንተ (ደህንነቶች ማለት ነው) እስረኞቻችሁን የምታስሯቸው የት ነው? ለብቻ ነበር?

🔹ተስፋዬ - አዎን፡፡ ለብቻ ነበር። የደርግ መርማሪዎች ትዕዛዝ የሚቀበሉት ከነተካ ቱሉ ነው፡፡ ከነሱ ትዕዛዝ እየተቀበሉ ይሠራሉ፡፡

🔸ገነት – ሥራቸው ከናንተ ጋር አይጋጭም?

🔹ተስፋዬ - ቢጋጭም በአንድ ማዕከል ኃላፊዎቻችን አንድ ናቸውና እነሱ ያስተካክሉታል፡፡ ምንም አይደለም፡፡

🔸ገነት – ማለት አንዱ ስለሰራው ከሌላው ጋር መረጃ የመለዋወጥ ሁኔታ?

🔹ተስፋዬ - ደርግ ጽህፈት ቤት ያለ መርማሪ ተራ ወታደር ፖሊስ ራሱን ልክ እንደ ደርግ አባል አድርጎ ስለሚቆጥር እኔ እንኳን አንድ ነገር ብጠይቀው ለመተባበር ፈቃደኛ አይሆንም፡፡ እሺ አይሉንም።

🔸ገነት - በኢንፎርሜሽን ደረጃም ቢሆን እርስዎ ስለኃይሌ ፊዳ አሟሟት የሚያውቁት ምንድነው?

🔹ተስፋዬ - መያዛቸውንና ደርግ ጽህፈት ቤት መታሠራቸውን አውቃለሁ፡፡ ያው እዛው መሆናቸውንና እዛ እንደነበሩ አውቃለሁ፡፡ በኋላ ላይ ኢሠፓኮ ሲመሠረት ሁለቱ የምርመራ ክፍሎች ተዋሃዱ - የደርግ ምርመራ ክፍልና የማዕከላዊ ምርመራ ክፍል፡፡ በትዕዛዝ ነው እንዲዋሃዱ የተደረገው፡፡ሌተናል ኰሎኔል መንግሥቱ አላውቅም ላሉት እሳቸው ሳያውቁ የሚሠራ አንዳችም ነገር የለም፡፡ትክክለኛውን ነገር አላውቅም እንጂ ደርግ ያሠራቸውን ሰዎች፣ ባለሥልጣኖችን፣ በተለይም ኃይሌ ፊዳን እዛው የታሰረበት ድረስ ሄደው ሳያነጋግሩ አልቀሩም፡፡ ኩዴታ የሞከሩትንም ጄኔራሎች የታሰ ሩበት ሄደው አነጋግረዋቸዋል፡፡

🔸ገነት – እርስዎ አብረዋቸው ይሄዳሉ?

🔹ተስፋዬ - እኔ አልሄድም፡፡ ወሬ ግን እሰማለሁ፡፡

🔸ገነት – የልዑል አሥራተ ካሣ ቤት እስር ቤት መሆኑን አላውቅም የሚሉትስ?

🔹ተስፋዬ - እሳቸው ይሄንን ቢሉም ከሳቸው ዕውቀት ውጪ በውነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ አንድም ነገር የለም፡፡ እሳቸው ሳያውቁ ምንም አይፈፀምም።

🔸ገነት -እርስዎ የሚያውቁት ነገር የለም? እኛ ስናይ አፅም እየተቆፈረ ሲወጣ፤ «ማነው የገደላቸው?» ሲባል ደህንነት ነው የሚባለው :

🔹ተስፋዬ - እሱማ ይባላል፡፡ ኢሕአዲግ ከገባ በኋላ ዝርዝር ወጥቶ እንደዚያ የሚባል ነገር ወጥቷል፡፡ ስለዚህ ይሄ እንዴት በዝርዝር ተፈፀመ? ያዘዙትስ ክፍሎችና ኃላፊዎቻቸውስ? የአሥራተ ካሣ ቤት በጠቅላላው ለደህንነቱ ሥራ ማደራጃና መቀመጫ ቦታ እንዲሆን ተጠይቆ በመንግሥት በኩል ተፈቅዶ የተሰጠ ነው፡፡ ያ ለማዕከላዊ ምርመራ የተመደበ ነው፡፡ እነዚያ ሰዎች ማዕከላዊ ምርመራ ሆነው ሲሠሩ የሚያደርጉትን ሁሉ የደህንነት ሚኒስትሩ በዝርዝር ለማወቅ አይችልም፡፡

🔸ገነት – እኔ ለማወቅ የምፈልገው ያንን ቦታ ማን ነበር የሚጠቀምበት?

🔹ተስፋዬ - የማዕከላዊ ምርመራ፡፡ ከማዕከላዊ ምርመራ በፊት፣ ማለት ማዕከላዊ ከመዋቀሩ በፊት የደርግ ልዩ ኃይሎች(ስፔሻል ፎርስ) የሚቀመጡት እዚያ ነበር፡፡መጀመሪያ ደብረ ብርሃን ነበሩ፡፡ ከዚያ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ድንገት የሚፈጠር ነገር ቢኖር ተብሉ ለዚያ እንዲሆኑ ነበር እዚያ የሠፈሩት፡፡

🔸ገነት – በግልዎ በእርስዎ ሥር ባይሆንም፤ ለምሳሴ ብዙ እንሰማለን፡፡ አሁን የሚገደሉ ሰዎች ምናምን እርስዎ ምንድን ነበር የሚያውቁት?የነበረዎት ኢንፎርሜሽን ካለ ....

🔹ተስፋዬ - እንግዲህ አንዳንዱ ነገር እኔ ባውቅም፣ ባላውቅም የሆነ ነገር ቢሆንም፣ ለማንኛውም በክስ የቀረበ ስለሆነ ያንን የክሱን ሁኔታ የሚያዛባ ስለሆነ እዚህ ላይ ቢቆም፡፡

🔻የሌተናልኮለኔልመንግስቱትዝታዎች፤ገነትአየለ፤68-70

12/10/2025

Jelani presents “The Woven Train Setup” — where the journey begins on nature’s tracks. 🚆🤍🌿

04/10/2025

Complete bed art to the world 🌎❤️❤️❤️❤️

30/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Assefa Yimam Hawass, Weleli Zeru, Esayas Gotta

23/08/2025

Nokia Royal Mini 2025 arrives with a stunning 200MP camera and huge 18200mAh battery 👉

21/08/2025

Address

Atlas
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911508002

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Horse Riding posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share