25/08/2025
"እነሆ ንጉሳችን "
አዲስ ዓመት ባከበርን ቁጥር ልናስታውሰው የሚገባን ቅኝ ገዢዎች ያልቀየሩት የዘመን አቆጣጠር ታሪክ ነው::
ታላቁን ቁማር የበላችው የምስራቋ ኮኮብ ሀገራችን ኢትዮጵያ በነገስታቶቿ እና በሕዝቧ ብርታት ነበር::
ከ 15ኛው ከዘመን በፊት የታቀደው ታላቁ ቁማር:
1ኛ. መጀመሪያ መንግስታቸውን እናጥፋው ወይም እናዳክመው, ስልጣኔአቸውን ታሪካቸውን, ፊደላቸውን, የቀን መቁጠሪያቸውን, እናጥፋው
2.ለእኛ አላማ የሚመች ሌላ ታሪክ እንፃፍላቸው,/ ድሀ, የድሀ ድሀ, ጨለማው አህጉር ሁዋላ ቀር.. መሀይም.. ውዘተ/ ማን እንደሆኑ እኛ ስም እናውጣላቸው
3ኛ. መንግስታቸውን ካጠፋን በሁዋላ የባሪያ ንግድ በመጀመር ያለ ምንም ከልካይ የሰው ሀይል እንውሰድ.. ሀገራችንን እንገንባ
( 18 ሚሊዮን ወጣት አፍሪካውያን ተወሰዱ )
4ኛ. መንግስት ስለሌላቸው ተመልሰን ሄደን እኛ እናስተደዳራችሁ እናሰልጥናችሁ እንበላቸው :: መንግስታችንን ሀገራቸው ላይ እንመስርት..የኛን ባህል የኛን ቋንቋ እናስተምራቸው... ቅኝ እንግዛቸው
5ኛ. በጎሳ, በሀይማኖት, እንከፋፍላቸው...
ለምሳሌ ሩዋንዳን ቤልጄም ነች ቅኝ የገዛችው.. ያኔ ለዜጎች የተሰጠ መታወቂያ ሁቲ እና ቱሲ የሚል ነበር:: ከብዙ ዓመት በሁዋላ ለሚሊዎኖች እልቂት ምክንያት ሆነ::
6ኛ. ድሆች መሆናቸውን ከነገርናቸው በሁዋላ እንርዳችሁ ብለን ተመለሰን እንሂድ:: ዕድገታቸውን እንቆጣጠር.. እንዳይሰሩ የሚያደርግ እርዳታ እንስጣቸው.. ብድር እንስጣቸው..
7ኛ.. ሰላም እንዳይኖር እናድርግ.. እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ እንስራ, ተረጋግተው እንዳይኖሩ እናድርግ::
ምንም ይሁን ምን ጠንካራ መንግስት እንዳይኖር እናድርግ::
ይሄ ነበር ቁማሩ::
ይሄን ቁማር ሁሉም ቦታ ላይ ሲሳካላቸው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ አልሆነም::
ያኔ ኢትዮጵያ እንሆ ንጉሳችንን እየዘመረች ነበር::
ምክንያቱም አፍሪካ በሙሉ ንጉስ አልባ እና መንግስት አልባ አድርገውት ነበርና...
ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ
አይነካም ነፃነትሽ
ተባብረዋል አርበኞችሽ
ብርቱ ናቸው ተራሮችሽ
ድል አድራጊው ንጉሳችን
ይኑርልን ለክብራችን
ኢትዮጵያን ለመረዳት የአፍሪካን ታሪክ መረዳት ይጠቀማል::
አፍሪካን ለመረዳት ኢትዮጵያን መረዳት ይጠቀማል::
ኢትዮጵያ ቅኝ እንዳትገዛ የኢትዮጵያ "ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ነገስታቱን በማማከር በመፀለይ እና ሕዝቡን በማስተባበር ኢትዮጵያን ለድል አብቀተዋል::" / The politics of southern Africa / የተባለ መፅሐፍ ውስጥ በደቡብ አፍሪካ ፕርፌሰሮች የተፃፈ::
ከአድዋ ድል በሁዋላ በሰባት የተለያዩ አለማት ውስጥ በውጪ ዜጎች የአቢሲኒያ ቤ/ ክርስትያን የሚባሉ ቤ/እምነቶች ተቋቁመው እስካሁን ድረስ አሉ::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የእምነት ተቋም ብቻ ሳትሆን ለጥቁሩ እና ጭቆናን ለሚቃወም ሁሉ የነፃነት ምልክት በመሆን በዓለም ታወቀች::
የኢትዮጵያ አዲስ አመት የዘመን አቆጣጠሩን ቅኝ ገዢዎች ስላልቀየሩት ከዓለም የተለየ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው::
አፍሪካ ከቅኝ ግዛት በፊት የሚለዉን ታሪክ ሊንኩ እነሆ
https://youtu.be/We30uXDzq7s?si=PcH9yX88LqNt484t
አክባሪያችሁ
ፍሬአለም ሺባባው
In 1884, the fate of an entire continent was decided—without a single African voice in the room.This is the untold story of the Berlin Conference, where Euro...