Dr. Etsub poultry & goat's farm consultant

Dr. Etsub poultry & goat's farm consultant Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Etsub poultry & goat's farm consultant, Veterinarian, durame, hossana, sodo, Durame.

✍️በዴካልብ ዎይት (Dekalb White) እና በቦቫን ብራውን (Bovans Brown) መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው🎯AccuBreed ዴካልብ ዋይት (በቅርቡ በኢትዮጵያ ገበያ የ...
17/03/2026

✍️በዴካልብ ዎይት (Dekalb White) እና በቦቫን ብራውን (Bovans Brown) መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው🎯AccuBreed

ዴካልብ ዋይት (በቅርቡ በኢትዮጵያ ገበያ የቀረቡ) እና ቦቫንስ ብራውን ሁለቱም ታዋቂ ዶሮዎች ቢሆኑም ግን አንዳንድ ቁልፍ ልዩነቶች አሏቸው።

✅የእንቁላል ምርት ዴካልብ ዎይት በጥሩ ሁኔታ ከተያዙ በአመት በአማካይ ከ300 በላይ እንቁላሎችን በመስጠት በከፍተኛ የእንቁላል ምርታቸው ይታወቃሉ።
✅ቦቫንስ ብራውን በጥሩ ሁኔታ ከተያዙ በአማካይ በአመት 250-300 ያህል እንቁላሎችን ይጥላሉ።
✅የዴካልብ ዋይት (Dekalb Whites) የእንቁላል መጠን መካከለኛ ሲሆን እና ነጭ ቅርፊት ያላቸው እንቁላል ይጥላሉ።
✅በአንፃራዊ ቦቫንስ ብራውንስ ከዴካልብ ዋይት ነጫጭ እንቁላሎች ትንሽ የሚበልጡ ቡናማ እንቁላሎችን ይጥላሉ።
✅ባህሪ=> ዴካልብ በተረጋጋ ባህሪያቸው ይታወቃሉ። በቀላሉ ለመያዝ ምቹ ናቸው።
✅ቦቫንስ ብራውንስ ከዴካልብ ዋይት በትንሹ የበለጡ ቁጡ ናቸው።
✅ጤና=> ሁለቱም ደካልብ ዋይት እና ቦቫንስ ብራውን በአጠቃላይ ጤናማ ዶሮዎች ናቸው። ይሁን እንጂ ቦቫንስ ብራውንስ ከዴካልብ ዋይትስ በአንፃራዊ ለበሽታዎች ተቋቋሚ ናቸው።

📍በአጠቃላይ ሁለቱም ዴካልብ ዋይት እና ቦቫንስ ብራውን ለእንቁላል ዶሮ እርባታ ጥሩ ምርጫዎች ናቸው። ከፍተኛ ምርት እና ነጭ የእንቁላል ቅርፊት ያላቸውን ፈለገው ከሆነ ዴካልብ ዋይት (Dekalb Whites) የተሻለ ምርጫ ናቸው። በሽታን የበለጠ የሚቋቋሙ እና ትለቅ ያሉ ቡናማ የእንቁላል ቅርፊት ከፈለጉ ቦቫንስ ብራውን የተሻለ ምርጫ ነው።

ለበለጠ መረጃዎች :

ስልክ :0979931866

💊 የዶሮ መድኃኒቶች አጠቃቀም፦ሙያዊ ማብራሪያእነዚህን ሦስት መድኃኒቶች ( Oxytetracycline, Amprolium, እና Vitastress ) በአንድ ላይ ቀላቅሎ መስጠት በፍጹም አይመከርም...
04/03/2026

💊 የዶሮ መድኃኒቶች አጠቃቀም፦ሙያዊ ማብራሪያ

እነዚህን ሦስት መድኃኒቶች ( Oxytetracycline, Amprolium, እና Vitastress ) በአንድ ላይ ቀላቅሎ መስጠት በፍጹም አይመከርም። ለዚህም ዋና ዋናዎቹ ሳይንሳዊ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. የመድኃኒት መጋጨት (Drug Antagonism)፦

የሚሰራው በዶሮዋ ሰውነት ውስጥ ያለውን B1 (Thiamine) ስርጭት በመግታት የደም ተቅማጥ አምጪ ጥገኞችን (Coccidia) በመግደል ነው።
ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያለው B1 ይዟል።
* ስለዚህ ሁለቱን በአንድ ላይ ሲቀላቀሉ፣ ቫይታሚኑ የአምፕሮሊየሙን ስራ ሙሉ በሙሉ ያከሽፈዋል። ይህም ማለት ለደም ተቅማጥ የሚሰጠው ሕክምና ምንም ውጤት አይኖረውም ማለት ነው።

2. የኩላሊት ጫና እና መመረዝ (Renal Stress & Toxicity)፦

* መድኃኒቶች በሰውነት ውስጥ ተቀነባብረው የሚወገዱት በኩላሊት በኩል ነው። ሦስት የተለያዩ ኬሚካሎችን በአንድ ላይ ማዋሃድ በታመመች ዶሮ ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ለድንገተኛ የኩላሊት መድከም (Visceral Gout) ወይም ለመድኃኒት መመረዝ ሊዳርግ ይችላል።

3. የመድኃኒት መራራነት (Palatability)፦

* ሦስቱም መድኃኒቶች በአንድ ላይ ሲቀላቀሉ የውሃውን ጣዕም በጣም መራራ ያደርጉታል። ዶሮዎቹ ውሃውን መጠጣት ካቆሙ ደግሞ መድኃኒቱን አያገኙም፤ ይባስ ብሎም በሰውነት ፈሳሽ እጥረት (Dehydration) የመሞት ዕድላቸው ይጨምራል።

---

✅ ሙያዊ ምክረ-ሀሳብ (Recommendation)

እንደ ምልክቶቹ ዓይነት ሕክምናውን በቅደም ተከተል መስጠት የተሻለ ነው፦

1. የአይን እብጠት እና የመተንፈሻ አካል ችግር ካለ፦
+ ከ 3-5 ቀናት ይስጡ። (ይህ ጥምረት ደህንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ ነው)።

2. የደም ተቅማጥ (Coccidiosis) ምልክት ካለ፦
* ከላይኛው ሕክምና በኋላ ብቻውን ለ 3-5 ቀናት ይስጡ። (በዚህ ጊዜ ቫይታሚን በፍጹም አይሰጥም)።

#ማሳሰቢያ፦ መድኃኒት ከመስጠትዎ በፊት የዶሮዎቹን ቤት ንጽህና መጠበቅ እና የአየር ዝውውሩን ማስተካከል ለመድኃኒቱ ውጤታማነት ወሳኝ ነው።

#የዶሮእርባታ #የክትባትመርሃግብር #የእንስሳትጤና . etsub

28/02/2026
የፍየል ቤት አሰራር እንደ አካባቢው የአየር ንብረት እና እንደ አቅም ቢለያይም፣ ጤናማ እና ምርታማ ፍየሎችን ለማርባት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።1. የቤት ዓይነት (H...
22/02/2026

የፍየል ቤት አሰራር እንደ አካባቢው የአየር ንብረት እና እንደ አቅም ቢለያይም፣ ጤናማ እና ምርታማ ፍየሎችን ለማርባት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።
1. የቤት ዓይነት (Housing Type)
ፍየሎች እርጥበትን እና ቅዝቃዜን ስለማይወዱ ቤቱ ደረቅ መሆን አለበት። ሁለት ዋና አማራጮች አሉ፦

✅ከፍ ያለ ወለል ያለው ቤት (Raised Floor): ወለሉ ከመሬት ከ 0.5 እስከ 1 ሜትር ከፍ ብሎ ከእንጨት (ለታ) የሚሰራ ነው። ፍሳሾች እና ኩበት በክፍተቱ ወደ ታች ስለሚወርዱ ቤቱ ሁልጊዜ ደረቅ እና ንጹህ ይሆናል።
✅መሬት ላይ የሚሰራ ቤት (Deep Litter): መሬቱ ኮንክሪት ወይም ጠጠር ሆኖ በላዩ ላይ ድርቆሽ ወይም እንጨት ስብርባሪ ይነጠፋል። ይሄኛው አማራጭ አነስተኛ ወጪ ቢጠይቅም የማያቋርጥ ጽዳት ይፈልጋል።
2. ዋና ዋና መስፈርቶች
አንድ ጥሩ የፍየል ቤት የሚከተሉት ነገሮች ሊኖሩት ይገባል፦
✅አየር ማናፈሻ (Ventilation): በቤቱ ውስጥ አየር በነፃነት መዘዋወር አለበት። ነገር ግን ለከፍተኛ ብርድ እና ለከባድ ንፋስ በቀጥታ መጋለጥ የለባቸውም።
✅የቦታ ስፋት: በአማካይ ለአንድ ትልቅ ፍየል ከ 1.5 እስከ 2 ካሬ ሜትር ቦታ ያስፈልጋል።
✅የመኖ እና የውሃ ገንዳ: መኖው መሬት ላይ እንዳይባክን ከፍ ብሎ በተሰራ ገንዳ (Racks) ላይ መቅረብ አለበት።
✅ብርሃን: ቤቱ በቂ የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝበት መሆን አለበት (ለቫይታሚን ዲ እና ባክቴሪያን ለመግደል)።
3. የቤት ክፍፍል (Categorization)
ሁሉንም ፍየሎች በአንድ ላይ ከማስቀመጥ ይልቅ እንደየባህሪያቸው መለየት ለጤንነታቸው ይመከራል፦
✅የመውለጃ ክፍል: እርጉዝ ፍየሎች የሚቆዩበት።
✅የልጆች ክፍል: ትናንሽ ልጆች የሚቆዩበት።
✅የጥሬ (ተባዕት) ክፍል: ጠንካራ ሽታ ስላላቸውና ሌሎችን እንዳይጎዱ ተለይተው ቢቀመጡ ይመረጣል።
✅የታመሙ ክፍሎች (Isolation): በሽታ እንዳይዛመት።
4. ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች
በአካባቢው በቀላሉ የሚገኙ ቁሳቁሶችን መጠቀም ወጪን ይቀንሳል፦
✅ምሰሶ: የባህር ዛፍ ወይም ጠንካራ እንጨት።
✅ጣሪያ: ቆርቆሮ፣ ሳር ወይም የዘንባባ ቅጠል። (ቆርቆሮ ከሆነ ሙቀት እንዳይበዛባቸው ከስሩ ሳር ቢነጠፍ ይመረጣል)።
✅ግድግዳ: እንጨት፣ የቀርከሃ አጥር ወይም ጡብ።
ጠቃሚ ምክር 💡
የፍየል ቤት ሲሰሩ የቤቱን አቅጣጫ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ቢያደርጉት የጠዋት ፀሐይን ለማግኘትና ከባድ ንፋስን ለመከላከል ይረዳል።

22/02/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! ወንጀለኛው ዳኛ, حكمة تمام

📢 አዲስ ራዕይ ለእንስሳት ጤና፦ "ህክምናው ከብቶቹን ይከተል!"የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎቻችን በየቀኑ የሚጋፈጡት አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ባለሙያውን ምን ያህ...
20/02/2026

📢 አዲስ ራዕይ ለእንስሳት ጤና፦ "ህክምናው ከብቶቹን ይከተል!"

የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎቻችን በየቀኑ የሚጋፈጡት አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ባለሙያውን ምን ያህል እንደሚወድና እንደሚፈልግ! ባለሙያ ከቦታው ሲጠፋ በህዝቡ ውስጥ የሚፈጠረው ጭንቀት የሙያችንን አስፈላጊነት በተግባር ያሳያል።

ነገር ግን አገልግሎታችን አሁንም ባለበት የቆመ (Stationary) ነው። አርብቶ አደር አከባቢዎች አርብቶ አደሩ ለግጦሽና ለውሃ ሲሰደድ፣ ከብቶቹ በሄዱበት ህክምናና ክትባት ማግኘት አለባቸው። ለዚህ ደግሞ "ተንቀሳቃሽ የቨተርነሪ አገልግሎት" (Mobile Veterinary Service) አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው!

ይህ ለውጥ እንዲመጣ ግን ስሜታዊ መሆን ብቻ በቂ አይደለም፤ የሚከተሉት መሠረታዊ "ቅድመ ሁኔታዎች" መሟላት አለባቸው፦

1ኛ. ለባለሙያው ክብርና ጥቅማጥቅም (Welfare): ባለሙያው ከቢሮ ወጥቶ ሜዳ ላይ እንዲውል ልዩ የሜዳ አበል (Hardship Allowance)، የህይወት መድን (Insurance) እና ምቹ ተንቀሳቃሽ መኖሪያዎች ሊመቻቹለት ይገባል። ባለሙያውን ሳይንከባከቡ እንስሳቱን ተንከባከብ ማለት አይቻልም!

2ኛ. የትጥቅና የቴክኖሎጂ አቅርቦት: ለቦታው የሚመጥኑ 4x4 ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች፣ በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ ተንቀሳቃሽ የክትባት ማቀዝቀዣዎች (Solar Cold Chain) እና ፈጣን የመመርመሪያ መሣሪያዎች (Field Kits) ለባለሙያው መቅረብ አለባቸው።

3ኛ. የአሰራርና የህግ ማዕቀፍ: አገልግሎቱ በዘፈቀደ ሳይሆን በህግና በመመሪያ የታገዘ የመድሃኒት ብክነትን የሚከላከልና የባለሙያውን ተጠያቂነትና መብት የሚያስከብር መዋቅር ሊኖረው ይገባል።

4ኛ. የደህንነት ዋስትና: ባለሙያው ራቅ ባሉ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የማህበረሰቡና የመንግስት ጥበቃ ሊታከልበት ይገባል።

ለምን አስፈለገ፦?

1️⃣ የወቅቱ ጥያቄ በመሆኑ፦ ልክ እንደ ዘላን ትምህርት ቤቶች፣ ህክምናውም የእንስሳቱን ፍልሰት መከተል አለበት።
2️⃣ በሽታን ለመግታት፦ ቁጥጥር ሳይደረግላቸው የሚንቀሳቀሱ እንስሳት በሽታን ያሰራጫሉ። ህክምናው አብሯቸው እንዳይንቀሳቀስ ግን ስርጭቱን ባለበት መግታት ይቻላል።
3️⃣ አርሶ አደሩን ለመታደግ፦ "ባለሙያ በሄድንበት ቢከተለን አንሰደድም ነበር" የሚሉ አርሶ አደሮች አሉ።

የሙያ ጓደኞቼ! እኛም አሰራራችንን ለማዘመን ዝግጁ መሆን አለብን። መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ደግሞ ባለሙያውን በማስታጠቅና መብቱን በማክበር ለዚህ ታሪካዊ ለውጥ መንገድ ሊከፍቱ ይገባል!

"ጤናማ እንስሳ — የበለጸገ አርሶ አደር — የጠንካራች ሀገር!" 🇪🇹

🚨 "ዝምተኛው አደጋ፦ AMR እና የነገው ትውልድ እጣ ፈንታ!"ዛሬም የማወራው ጉዳዩ በጣም አስከፊና ችላ ሊባል የማይገባ፣ ነገር ግን በሚያሳፍር መልኩ ትኩረት ተነፍጎት ሳይታወቅበት ስር እየሰ...
20/02/2026

🚨 "ዝምተኛው አደጋ፦ AMR እና የነገው ትውልድ እጣ ፈንታ!"
ዛሬም የማወራው ጉዳዩ በጣም አስከፊና ችላ ሊባል የማይገባ፣ ነገር ግን በሚያሳፍር መልኩ ትኩረት ተነፍጎት ሳይታወቅበት ስር እየሰደደ ያለ፣ በእያንዳንዳችን ህይወት ላይ የተደገነ አደጋ ስለሆነ ነው።
ስለ AMR (የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ) አደገኝነት ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ፖስት አድርጌያለሁ፣ ዛሬም ግን ደግሜ እጮኻለሁ! ይህ ጉዳይ በሚዲያም ሆነ በሚመለከታቸው አካላት በቂ ትኩረት አለማግኘቱ እጅግ አደገኛ ነው።
ህዝቡ (አርሶ አደሩ) ስለ AMR አስከፊነት ባለማወቅ የእንስሳት መድኃኒቶችን እንደሚከተለው ሊያባክን ይችላል፦
በግምት የሚሰጥ ሕክምና (Empirical treatment)፦ በሽታው በላብራቶሪ ሳይለይ፣ ዝም ብሎ የሚገኘውን አንቲባዮቲክ ለሁሉም በሽታ በመውጋት መድኃኒቱን ለብክነት ይዳርጋል።
ለክብደት መጨመሪያ መጠቀም (Growth Promotion)፦ እንስሳቱ ሳይታመሙ፣ ለሥጋና ለወተት ምርት መጨመሪያ ተብሎ አንቲባዮቲክ በመኖ ውስጥ ሲቀላቀል መድኃኒቱ ለታለመለት የሕክምና ዓላማ ሳይሆን ለብክነት እየዋለ ነው።
የመድኃኒት መጠን ስህተት (Wrong Dosage)፦ ለአንድ እንስሳ መሰጠት ያለበትን መጠን ቀንሶ መውጋት ወይም ለአንድ ቀን ብቻ ወግቶ መተው መድኃኒቱን ከማባከንም ባለፈ ባክቴሪያው መድኃኒቱን እንዲለምደው (Resistance) በር ይከፍታል።
እኛ ግን የምናውቀው ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከተን የመንግሥት አካላት ለምን ዝምታን መረጥን? ዛሬ በየገበያው ያለ ባለሙያ ትእዛዝ (Prescription) አንቲባዮቲኮች እንደ ከረሜላ ሲታደሉ እያየን ዝም ማለታችን የነገውን ትውልድ ሕክምና ወደማይገኝለት ደዌ አሳልፎ መስጠት ነው።
ጥያቄዬ ለሚከተሉት አካላት ነው፦
ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA)፦ ያለ ባለሙያ ትእዛዝ የሚታደለውና ለAMR መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት የሆነው መድኃኒት ቁጥጥሩ የት ደረሰ?
ለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን (Ethiopian Agriculture Authority)፦ በእንስሳት መድኃኒት አያያዝ እና በምርቶች ላይ በሚቀረው የመድኃኒት ቅሪት (Residue) ላይ ያለው ቁጥጥር ለምን አልጠነከረም?
ለኢትዮጵያ የእንስሳት ሕክምና ማህበር (EVA)፦ ማህበሩ ይህንን አገራዊ ስጋት ለመከላከል ባለሙያውን ከማነቃቃትና ፖሊሲ አውጪዎችን ከመጫን አንጻር ለምን ድምፁ ጠፋ?
ለግብርና ሚኒስቴር (MoA)፦ ዘርፉን ራሱን አስችሎ ለAMR ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ መዋቅር አለመኖሩ ለችግሩ መባባስ ምክንያት መሆኑን ተረድታችሁታል?
ባለሙያ ባልደረቦቼ ሆይ! ዝምታችን ተባባሪነት ነው። ነገ ልጆቻችን የታዘዘላቸው መድኃኒት ሳይፈውሳቸው ሲቀር የታሪክ ተጠያቂዎች እኛው ነን። ነገም ወደፊትም ችግሩ ትኩረት አግኝቶ እስኪቀረፍ ድረስ እጮሀለሁ! እንጮሀለን!
ድምፃችንን እናሰማ! ይህ መልዕክት ለሚመለከተው አካል እስኪደርስ Share በማድረግ እና ተቋማቱን Tag በማድረግ ተባበሩ!

📲 ተጨማሪ ሙያዊ ምክሮችን እና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👇 https://t.me/volentervetcare

መምህር፣ ክትባት ከሰጠን በኋላ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ወይ? ምን ማድረግ አለብን? 🤔💉🐑በቅርቡ አንድ የእንስሳት ጤና ባለሙያ ያጋራኝ አሳዛኝ ገጠመኝ፣ የባለሙያ አያያዝን እና የአርሶ አደሮች...
17/02/2026

መምህር፣ ክትባት ከሰጠን በኋላ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ወይ? ምን ማድረግ አለብን? 🤔💉🐑

በቅርቡ አንድ የእንስሳት ጤና ባለሙያ ያጋራኝ አሳዛኝ ገጠመኝ፣ የባለሙያ አያያዝን እና የአርሶ አደሮችን ግንዛቤ ለማሳደግ ወሳኝ ትምህርት ይዟል። ለሌሎቻችሁም መማሪያ ይሆን ዘንድ የባለሙያውን ጥያቄ ከምላሽ ጋር እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፦

የባለሙያው ጥያቄ፦

"በምሰራበት ቀበሌ ክትባት ሰጥቼ ከጨረስኩ በኋላ፣አንድ አርሶ አደር 'ከብቶቼን የፈጀኸው አንተ ነህ፣ ክትባት ብለህ ከወጋሃቸው በኋላ ነው ታመው የሞቱብኝ' ብሎ ከሰሰኝ። እኔ ግን ክትባቱን በአግባቡ መስጠቴን እርግጠኛ ነኝ። ምን ሊሆን ይችላል?"

ምላሽ እና ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

እንደ አንድ የእንስሳት ሐኪም፣ ይህ አሳዛኝ አደጋ ለምን እንደሚከሰት እና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ዋና ዋና ምክንያቶችን እንደሚከተለው አብራራለሁ፦

1️⃣ የክትባቱ ጥራት መበላሸት (Cold Chain Failure)፦ ክትባቱ ከማቀዝቀዣው ከወጣ በኋላ፣ ተወግቶ እስኪያልቅ ድረስ ቀዝቃዛ ሆኖ ካልቆየ ውጤት አልባ ሊሆን ይችላል።

2️⃣ እንስሳቱ አስቀድመው መታመማቸው፦ እንስሳቱ ክትባቱን በሚወጉበት ወቅት አስቀድመው በበሽታው ተይዘው ከሆነ፣ ክትባቱ በሽታውን ሊያባብሰው ይችላል።

3️⃣ ከክትባት በኋላ እንስሳቱን ማስጨነቅ (Stress)፦ ከተከተቡ በኋላ እንስሳቱ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከገቡ ለምሳሌ ረጅም ጉዞ ከተጓዙ የክትባቱን ውጤት መቋቋም አይችሉም።

⚠️ የባለሙያው ድርሻ ሊሆኑ የሚችሉ ስህተቶች (በተጨባጭ ሁኔታ)፦

የክትባት ማቀዝቀዣ (Cold Chain) መቋረጥ፦ በሀገራችን ሁሉም በሚባል ደረጃ የቀበሌ ጤና ኬላዎች ማቀዝቀዣ ዬላቸውም፣ ክትባቶች ደግሞ ያለማቀዝቀዣ ከተቀመጡ ይበላሻሉ፣ ጥቅም አልባ ይሆናሉ።

የተበላሸ ክትባት መስጠት፦ ማቀዝቀዣ በሌለበት ሁኔታ፣ በተለይም ክትባቱ ከተከፈተ በኋላ በዚያው ቀን ውስጥ ካላለቀ፣ ውጤታማነቱን ሙሉ በሙሉ ያጣል። ከተከፈተ በኋላ የቀጣዩን ቀን ክትባት ቢያንስ ወደ ወረዳ ማዕከል ማቀዝቀዣ መመለስ አለመቻል ክትባቱ እንዲበላሽ ወይም እንዲበከል ያደርጋል።

የክትባት አሰጣጥ ዘዴ ስህተት፦ በተለይ የቆዳ ስር (Subcutaneous) ክትባቶች ወደ ቆዳው ስር በደንብ ዘልቀው ሳይገቡ በቆዳው ላይ ቢፈሱ፣ ክትባቱ በትክክል አይሰራም።

የመጠን ስህተት (Dosage Error)፦ የተፈቀደው መጠን ሳይሆን በጣም አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መጠን መስጠት እና የመሳሰሉት ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

✅ መፍትሄው፦

ክትባቱ በአግባቡ መቀዝቀዙን ያረጋግጡ።

ጤናማ እንስሳትን ብቻ ያስከተቡ።

ከክትባት በኋላ እንስሳቱን በጥሩ ሁኔታ ይያዙ።

ተመሳሳይ ችግር ሲገጥም ወዲያውኑ ለወረዳ ወይም ለዞን ባለሙያዎች ሪፖርት አድርገው ምርመራ እንዲደረግ ያድርጉ።

💡 ለአርሶና አርብቶ አደሮቻችን ምክር፦

"በሽታን ከማከም መከላከል ይበልጣል! ክትባት የንብረትዎ ዋስትና ነው። የክትባት ከላንደርን በማክበርና ሳይዘናጉ በማስከተብ እንስሳትዎን ከሞት፣ኢኮኖሚዎን ከኪሳራ ይታደጉ። ምንም እንኳ ተመሳሳይ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ባለሙያዎችን ያማክሩ እንጂ፣ ክትባትን ከማስከተብ ለአፍታም ቢሆን እንዳይዘናጉ።

"በአካባቢዎ ክትባት ከተሰጠ በኋላ እንስሳት ሲታመሙ ወይም ሲሞቱ ተመልክተው ያውቃሉ? ምን ያህል ጊዜ ወስዶባቸው ነው የሞቱት? አስተያየታችሁን በኮሜንት ላይ
ምንጭ (volenter Vet.care)

ጉምቦሮ የዶሮ በሽታ (Gumboro Disease)የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ከስጋ ዶሮዎች በላይ የሚያጠቃ በሽታ✨በመላው አለም ላይ የሚገኝ የዶሮዎች በሽታ ሲሆን በሌላ ስሙ ኢንፌክሽየስ ቡርሳል ...
07/02/2026

ጉምቦሮ የዶሮ በሽታ (Gumboro Disease)

የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ከስጋ ዶሮዎች በላይ የሚያጠቃ በሽታ

✨በመላው አለም ላይ የሚገኝ የዶሮዎች በሽታ ሲሆን በሌላ ስሙ ኢንፌክሽየስ ቡርሳል በሽታ( IBD) ይባላል። በመጀመሪያ በአውሮፓ የታየው በሽታ ቃስ በቃስ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ እየተንሰራፋ መጥቷል። ኢንፌክሽየስ ቡርሳል በሽታ( IBD) የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ከስጋ ዶሮዎች በላይ በጣም የሚያጠቃ በሽታ ነው።

የበሽታው መንስኤ

✨በሽታው ኢንፌክሽየስ ቡርሳል ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን ሌላም የቫይረሱ ዘረመል(gene) ስሙ ቢርና ቫይረስ (birna Virus) ይባላል። ከዶሮው ቡርሳ ፋብሪከስ (bursa Fabricus) ውስጥ ይገኛል። ሌሎች የዶሮ ሰውነት ክፍሎች ላይ ቫይረሱ ሊገኝ ይችላል።

የበሽታው ምልክቶች

✨ዶሮዎቹ ንቃት አይኖራቸውም፤ ውሀ የሚበዛበት ተቅማጥ ይኖራቸዋል፤ ላባቸው የገረጣ እና የደረቀ ይሆናል፤ የሰውነት ውሀ መጠናቸው በእጅጉ ይወርዳል። በሽታው በዋነኝነት ከ3-6 ሳምንት እድሜ ያላቸውን ዶሮዎች ያጠቃል። ከ3 ሳምንት በታች ያሉ ዶሮዎችን ቢያጠቃም ይህ ነው የሚባል የበሽታ ምልክት አያሳዩም። አያሳዩም ብንልም ግን የኋላ የኋላ በሽታ የመከላከል አቅማቸውን እንዲያጡ በማድረግ ለሌሎች ባክቴሪያ እና ቫይረስ በቀላሉ እንዲጋለጡ ያደርጋል። የስጋ ዶሮዎች ሊደርሱበት ከሚችለው 45 ቀናት ተጨማሪ አምስት ቀናት ከፍ ይላል። ክብደት የመያዛቸውን አቅም ይቀንሳል።

የበሽታው ህክምና

✨ምንም አይነት ህክምና የለውም። የሰውነት የመከላከል አቅማቸውን የሚጠናክር በእንስሳት ሀኪሙ በኩል መስጠት ብቻ ነው።

የመቆጣጠሪያ እና መከላከያ ዘዴ
ክትባት

1-21 ቀናት ውስጥ ክትባት የሚሰጥ ይሆናል። ቀደም ብሎ መስጠቱ ግን ወሳኝ ነው።
+251979931866

07/02/2026

Don’t retire and take your retirement benefits to farm tomato . That will be the easiest route to high blood pressure.

ሀሉም የሆነው በሂደት ነው፦ እያንዳንዱ አስተማሪ በአንድ ወቅት ተማሪ ነበር። እያንዳንዱ አሸናፊ በአንድ ወቅት ተሸናፊ ነበር። እያንዳንዱ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። በየቀኑ የምንወስ...
06/02/2026

ሀሉም የሆነው በሂደት ነው፦ እያንዳንዱ አስተማሪ በአንድ ወቅት ተማሪ ነበር። እያንዳንዱ አሸናፊ በአንድ ወቅት ተሸናፊ ነበር። እያንዳንዱ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። በየቀኑ የምንወስዳቸው ትናንሽ እርምጃዎች ወደ ስኬታማነት በሂደት ይመሩናል።

Address

Durame, Hossana, Sodo
Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Etsub poultry & goat's farm consultant posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dr. Etsub poultry & goat's farm consultant:

Share

Category