Ŵube Veterinary Ŝervice /ውቤ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ŵube Veterinary Ŝervice /ውቤ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት

Ŵube Veterinary Ŝervice /ውቤ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት እንኳን ወደ የፌስቡክ ገፃችን መጡ!
በዚህ ቻናል በባለሙያዎች የተደገፉ ስለ እንስሳት ጤና አጠባበቅ እና ቅድመ መከላከል መረጃዎች ይለቀቃሉ። መልካም ቆይታ!

08/03/2026

What is ur Diagnosis and Treatment?


08/03/2026
08/03/2026

Rabies vaccination at Adama 💉🐾🥰


ዝመተኞቹ ጀግኖች 🐾💛🐕በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለስልጣን (EWCA) እና በአፍሪካ የዱር እንስሳት ፋውንዴሽን (AWF) በመተባበር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚገኘ...
01/11/2025

ዝመተኞቹ ጀግኖች 🐾💛🐕

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለስልጣን (EWCA) እና በአፍሪካ የዱር እንስሳት ፋውንዴሽን (AWF) በመተባበር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚገኘው የውሻ ክፍል (Canine Unit)።

ይህ ክፍል ህገወጥ የዱር እንስሳት ዝውውርን ለመዋጋት እና ለተፈጥሮ ሀብቶቻችን ፍትህን ለማስፈን ወሳኝ ሚና ይጫወታል። መመስረቱ ኢትዮጵያ በዱር እንስሳት ጥበቃና ዘላቂ ልማት ላይ ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ ነው።

ይህ የውሻ ክፍል በይፋ በአምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር በጥቅምት 10 ቀን 2024 እ.ኤ.አ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

እኛም ከኤግል የእንስሳት ክሊኒክ ጋር በአብሮነት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሚሰሩ ህገወጥ የዱር እንስሳት ዝውውር ምርመራ ላይ የምሰሩትን ውሾች ጤና ለመጠበቅና ህክምና ለመስጠት በመመረጣችንና የዚ አካል በመሆናችን ክብር ይሰማናል። የእነዚህን ታታሪ ውሾች ጤናማ፣ ጠንካራ እና ለተልዕኳቸው ዝግጁ ሆነው እንዲቆዩ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን። 💪🐶

እያንዳንዱ ምርመራ፣ እያንዳንዱ የክትትል ክፍለ ጊዜ እና እያንዳንዱ ትንሽ የእንክብካቤ እርምጃ የአፍሪካን የዱር እንስሳት ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 🌍💚

በዶ/ር አልዓዛር አየለ

#የእንስሳትህክምና #ከተማሪነትበላይለለውጥ

01/11/2025
28/10/2025

ለውሾቻችሁ ህክምና እና የምክር አገልግሎት ከፈለጋችሁ በ0961951390 ይደውሉ

12/10/2025

#እንስሳትትኩረትይሻሉ #የእንስሳትህክምና

Today I had the honor of celebrating World Animal Day at Feven – Animals Need Attention Initiative, a shelter founded wi...
07/10/2025

Today I had the honor of celebrating World Animal Day at Feven – Animals Need Attention Initiative, a shelter founded with such a compassionate heart for animals in need.

We celebrated together with dogs who once lived on the streets of Addis Ababa, but today found love, care, and dignity. I also had the chance to voluntarily vaccinate 20 dogs against rabies — a small step to keep them and our community safe. 🐶💉

I’m truly inspired by Feven’s kindness and dedication. She not only rescues and shelters dogs but also cares for a brave donkey who survived cruelty and even hyena attacks. 🐴❤️

Her work is a shining example of compassion in action. 🙏✨

Let’s all remember: every animal deserves care, protection, and respect. 💚



የአለም የእንስሳት ቀን በእንስሳት ትኩረት ይሻሉ የእንስሳት ማቆያ !!!

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ በእንስሳት ትኩረትን ይሻሉ መስራች ፌቨን መለሰ የተከፈተውን የእንሳት ማቆያ (shelter) በጥቂቱ ልንገራችሁ። በዚህ የእንስሳት ማቆያ በጎዳና ላይ የነበሩ እና በተለያየ የአካል ጉዳት ላይ ያሉ ወደ 25 የሚጠጉ ውሾች ሲኖሩ በተጨማሪም ባለቤቶቿ ተጠቅመው የጣሏት ከጅብ ንክሻ የተረፈች አንዲት አህያ አለች። በእውነቱ ከሆነ በዚህ ቦታ ላይ በመገኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ኮርቻለሁም። ይህንን ስራ መንግስት መስራት ያለበት ስራ ሆኖ ሳለ በአንዲት ጎበዝ ፣ ጠንካራ እና ሩህሩህ ልብ ያላት እንስት መከፈቱ የሚያስመሰግን እና ሊበረታታ የሚገባው ተግባር ነው።

መስከረም 24 የተከበረውን የአለም እንስሳት ቀን ምክንያት በማድረግ እኔ በበኩሌ የራሴን አሻራ ለማሳረፍ መጠለያው ውስጥ ያሉ ውሾትን የውሻ እብደት በሽታ በተሳካ ሁኔታ ከትቤያለሁ። ከዚህ በተሻለ ደግሞ እንደ አንድ ግለሰብ እና የእንስሳት ጤና ባለሙያ ይህንን የተቀደሰ ሃሳብ በተቻለ መጠን ለማገዝ ከፈጣሪ ጋር የቻልኩትን አደርጋለሁ።

እንዲህ ያለ መጠለያ (shelter) በእንስሳት ደህንነት ላይ ትልቅ ሚና አለው። ይህም እንስሳትን ከጎዳና ሕይወት ያወጣል፣ በበሽታ እና በተለያዩ አካላዊ ጥቃት የተጎዱትን ያድናል፣ የተመቻቸ ህክምና እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ያደርጋል እንዲሁም በዋነኝነት ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር እና በጎዳና ላይ ያሉ የእንስሳትን ቁጥር በመቀነስ ለሰው እና ለእንስሳት ደህንነት ይረዳል። 🏠💚

በእውነቱ ፌቨን ለጀመረችው ነገር ትልቅ አክብሮት አለኝ። የበለጠ አድጎ ትልልቅ ነገሮች እንደሚኖሩት ተስፋ አደርጋለሁ በርቺ ለማለትም እወዳለው። ይህን ፅሁፍ የምታነቡ ፌቨንን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች "እንስሳት ትኩረትን ይሻሉ"( Animals Need Attention) ብላችሁ በመፈለግ ማግኘት ትችላላችሁ።

ይህንን እናስታውስ "ማንኛውም እንስሳ ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ክብር ይገባዋል።"

በዶ/ር አልአዛር አየለ
#የአለምእንስሳትቀን
#እንስሳትትኩረትይሻሉ

Address

Gizaw Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:00

Telephone

+251961951390

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ŵube Veterinary Ŝervice /ውቤ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ŵube Veterinary Ŝervice /ውቤ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት:

Share

Category