እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ

እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ If you want to support please dm🙏

Animals need attention is a charity fighting for animals right, promote responsible pet ownership , creating community awarness, shelter, medical treatment,Implementing spay and neuter,rescuing ,promote animal welfare .

Feven Melese
20/08/2025

Feven Melese

17/08/2025

Give them A Second Chance: Compassion and Care for All Animals

Animal Needs Attention Initiatives has been working for the past seven years to protect and promote animal welfare. Our efforts include:

Advocating for animal rights and creating community awareness.

Organizing feeding programs for homeless dogs and cats, and establishing permanent feeding stations in different areas.

Providing rabies vaccinations to street dogs to prevent the spread of disease.

Implementing spay and neuter projects to control the stray dog population.

Supporting adoption programs to help homeless animals find loving families.

Rescuing and treating sick and abounded animals from the streets. We have given thousands of animals hope and life.

But today, our mission needs you more than ever. We are opening a new animal shelter to give even more animals safety, healing, and love.

🙏 Your support can save lives:

💰 Donate funds to keep our programs alive.

🥫 Contribute food or medical supplies.

❤️ Sponsor an animal’s care.

Together, we can make sure no animal is left behind.

1000099001716
Cbe

https://www.paypal.me/YeabtsegaAsres

Feven Melese founder&CEO

ቡችላዎን ደስተኛ ፣ ጤናማ ህይወት ይስጡት!!!1. የተመጣጠነ ምግብ ✔ ጥሩ የውሻ ምግብ  ይመግቡት: የተቀቀለ ዶሮ፣ ሩዝ፣ አትክልት፣ እርጎ✔ የመመገቢያ መርሃ ግብር: * 6-12 ሳምንታት: ...
09/08/2025

ቡችላዎን ደስተኛ ፣ ጤናማ ህይወት ይስጡት!!!

1. የተመጣጠነ ምግብ
✔ ጥሩ የውሻ ምግብ ይመግቡት: የተቀቀለ ዶሮ፣ ሩዝ፣ አትክልት፣ እርጎ
✔ የመመገቢያ መርሃ ግብር:
* 6-12 ሳምንታት: 4 ምግቦች / ቀን
* 3-6 ወራት: 3 ምግቦች / ቀን
* 6+ ወራት: 2 ምግቦች / ቀን
✔ ንጹህ ውሃ ሁል ጊዜ ያቅርቡ።
❌ እንደ ቸኮሌት፣ አጥንት፣ ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርት ያሉ ጎጂ ምግቦችን ያስወግዱ።

2. የክትባት እና ፀረ-ትላትል መርሃ ግብር
📌 ከ2 ሳምንታቸው ጀምሮ እስከ 6 ወር እድሜያቸው ድረስ በየ2 ሳምንቱ ፀረ ትላትል እንዲያገኙ ማድረግ
📌ከ6-8 ሳምንታት፡ የመጀመሪያ ክትባቶች (intial Dose) (ፓርቮ፣ ዲስቴምፐር፣ ወዘተ)።
📌 9–12 ሳምንታት፡ የማጠናከሪያ ክትባቶች (Booster Dose)
📌 12+ ሳምንታት፡ የእብድ ውሻ ክትባት (ግዴታ)።
📌6 ወር ሲሞላቸው በየ 2 ወሩ ፀረ-ትላትል መስጠት ።

3. ንጽህና እና የፀጉር አያያዝ
✔ ለቡችላ በየ 2 ሳምን ለትልልቆች በ 2 ወር አንድ ጊዜ በውሻ ሻምፑ ይጠቡዋቸው።
✔ ፀጉራቸውንን ያበጥሩ እና ጥፍሮቻቸውን ይቀንሱ።
✔ ጆሮዋቸውን ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር ንፅህናውን ያረጋግጡ።

4. ስልጠና እና ማህበራዊነት
✔ መሰረታዊ ትእዛዞችን ቀድመው ያስተምሩ (ተቀመጡ ፣ ቁጭበሉ ፣ ይምጡ እና የመሣሠሉ) ።
✔ ከሰዎች እና ከሌሎች የቤት እንስሳት ጋር ይገናኙ።
✔ ካላስፈላጊ ጥፋት ለመዳን ለጥርሶች ማኘክ መጫወቻዎች በማቅረብ ቢዚ ያርጓቸው።

5. የእንስሳት ህክምና
✔ ጤናማ ቡችላ እንዲኖሮ የእንስሳት ሐኪም ምርመራ ያድርጉ።
✔ በተገቢው እድሜያቸው ላይ እንዳይወልዱ የሚፈልጉ ከሆነ ያስመክኑ።

6. በውሻ ላይ የሚስተዋሉ ጭካኔዎች እና ውጤቶቹ:

6.1. አካላዊ ጥቃት፡- በመምታት፣ በሌሎች የጥቃት ዓይነቶች ጉዳት ማድረስ።

6.2. ችላ ማለት፡- መሰረታዊ ፍላጎቶችን እንደ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ፣ እና ህክምና ማቅረብ አለመቻል።

6.3. ማሰር፡- ውሾችን ያለ በቂ ቦታ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ማህበራዊ ግንኙነት ሳያደርጉ ለረጅም ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ ማድረግ።

6.4. ከመጠን በላይ መራባት፡-ለትርፍ ወይም በቸልተኝነት ውሾችን ከልክ ያለፈ ከተራቡ ለጤና ችግር እና ለስቃይ ይዳርጋቸዋል።

የጭካኔ ተግባሮቹ ውጤቶች :

‼️ የጤና መታወክ፡- ለጭካኔ የተዳረጉ ውሾች በአካል ጉዳት፣ በምግብ እጥረት፣ ህክምና ባለማግኘት፣በህመም እና ጥገኛ ተህዋሲያን ሊሰቃዩ ይችላሉ፣ ይህም ወደ ሥር የሰደደ የጤና ችግር እና ሞት እንዲከሰት ያደርጋል።

‼️ የባህሪ ችግሮች፡- የጭካኔ ድርጊቶች ሰለባ የሆኑ ውሾች ብዙውን ጊዜ እንደ ጠበኝነት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ወይም መደበቅ ያሉ የባህሪ ሁኔታዎችን ያዳብራሉ። እነዚህ ጉዳዮች እነሱን ለመቀበል ወይም ለመንከባከብ አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል እና ወደ ማጎሳቆል ሊያመራቸው ይችላል።

‼️ የስሜት ጭንቀት፡- ጭካኔ በውሾች ላይ የረዥም ጊዜ የስነ ልቦና ጉዳት ያስከትላል፣ ይህም ወደ ጭንቀት፣ ድብርት እና በሰው ላይ እምነት ማጣትን ያስከትላል።

‼️ የጥቃት መጨመር፡- በደል የሚደርስባቸው ወይም ችላ የተባሉ ውሾች ከፍርሃት ወይም ከብስጭት የተነሳ ጠበኛ ሊሆኑና ይህም በሰዎች እና በሌሎች እንስሳት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ ይህ ብዙ ንክሻዎችን እና ጥቃቶችን በእንስሳትም ሆነ በማህበረሰቡ ላይ ያስከትላል።

‼️ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ውሾች ለረጅም ጊዜ ታስረው ለከፍተኛ የአካል እና የስነልቦና ጭንቀት ይዳርጋሉ። ይህ ድርጊት ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውጪ ስለሚያደርጋቸው የታሰሩ ውሾች በፍርሃትና በጭንቀጥ ምክንያት ጠበኛ እና ተናካሽ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ረዘም ላለ ጊዜ መታሰር የአካል ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል፣ ለምሳሌ ለረጂም ጊዜ በአንገት ቀበቶ የታሰረ ውሻ ቆስሎበት ለተለያዩ ጥገኛ ተህዋሲያን በማጋለጥ ለአጠቃላይ ጤና መጓደል አስተዋጽኦ ያደርጋል።

‼️ ጎዳና ውሾች መብዛት፡- ብዙ ጊዜ በተገቢ መንገድ ያልተንከባከብናቸው ውሾች ወይም ያልመከኑ ውሾች ያለ ቁጥጥር ስለሚራቡ የጎዳና ውሾች እንዲበዙ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

እንዴት አድርገን ጭካኔውን እንከላከል:

🐾 ትምህርት በመስጠት፡ ስለ ሰብአዊ የውሾች ሆነ እንስሳት አያያዝ፣ ኃላፊነት የሚሰማው የቤት እንስሳት ባለቤትነት እና የጭካኔ ውጤቶች ግንዛቤን ማሳደግ የውሻ ጥቃትን ለመቀነስ ይረዳል።

🐾ህግ፡ ጠንከር ያሉ የእንስሳት ጥበቃ ህጎችን መደገፍ እና ያሉትን ደንቦች መተግበር የጭካኔን ድርጊቶች ለመከላከል ይረዳል።

🐾ሰዎች ውሾችን በመግዛት ፋንታ መንገድ ላይ ያሉትን እንዲያሳድጉ ማበረታታት ለውሾች የበለጠ ርህራሄን እኔ ቤተሰብ እንዲኖራቸው ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

🐾❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️
ፍቅርን፣ ትዕግስትን እና አስተማማኝ ቤትን ለቡችላዎ ያቅርቡ ቡችላዎም ዕድሜ ልክ ታማኝነትን ይሰጥዎታል!
❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️🐾❣️❣️

አልዓዛር አየለ የዉቤ ልጅ

እንስሳት በሰው ልጆች የጭካኔ ድርጊት ሲፈፀምባቸው ቆሞ ማየት እና ከንፈር መጦ ማለፍ ጥቃቱን እንደመደገፍ እና ለአጥቂው እውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል!!ጀግኖች ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ም...
03/08/2025

እንስሳት በሰው ልጆች የጭካኔ ድርጊት ሲፈፀምባቸው ቆሞ ማየት እና ከንፈር መጦ ማለፍ ጥቃቱን እንደመደገፍ እና ለአጥቂው እውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል!!

ጀግኖች ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ምስጊን የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሲሰቃዩ ሲያዩ መከታ ይሆኗቸዋል እንጂ አንደበታቸውን ለጉመው ችላ ብለው አያልፉም።

ለእንስሳት መብት የሚታገል እና የእነሱን መብት የማይቀማ ትውልድ መፍጠር ስንጀምር በተዘዋዋሪ የእኛንም መብት የሚያከብር ትውልድ ፈጠርን ማለት ነው።

Feven Melese
https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8yYverLZRIc&_r=1

follow my page 🙏

ሼልተር ለሚገቡት ውሾች የተገዛ መተኛ ነው። ግን እንጨቱ ስለሚቆረቁራቸው አሮጌ ፍራሾችም ቢሆኑ ያስፈልጋቸዋል 🙏 ስለዛ አሮጌ ወይም የማትፈልጉት ፍራሽ /ስፖንጅ/ ካላችሁ መስጠት ትችላላችሁ። ...
30/07/2025

ሼልተር ለሚገቡት ውሾች የተገዛ መተኛ ነው። ግን እንጨቱ ስለሚቆረቁራቸው አሮጌ ፍራሾችም ቢሆኑ ያስፈልጋቸዋል 🙏 ስለዛ አሮጌ ወይም የማትፈልጉት ፍራሽ /ስፖንጅ/ ካላችሁ መስጠት ትችላላችሁ።

የተሻለ ህይወት በጎዳና ላሉ እንስሶች ያስፈልጋቸዋል
እንስሳትም ትኩረት ይሻሉFeven Melese

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251913585438

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ:

Share